Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የሰንደቅ አላማ ቀን በመከበር ላይ ነው

flag-day-celebration
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከበር የሃገራችን ብሔራዊ ጥቅም ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት የተሳተፉ አካላትን በመታገልና ለህግ አሳልፎ በመስጠት መሆን እንዳለበት ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ ለዘጠነኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን የስንደቅ ዓላማ ቀን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ከታሪካችን የነፃነታችን አርማ፤ ከብዝሃነታችን በመፈቃቀድ ላይ ለመሰረትነው የዲሞክራሲ አንድነታችን ስንደቅ ዓላማችን መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ለሃገሩ ስላም ርብርብ እንዲያድርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ስንደቅ ዓላማችን በዓለም ላይ ከፍታው እየጨመረ መጥቷል ያሉት ፕሬዚዳንት ሙላቱ፥ ይህም የኢትዮጵያ ህዝቦች በድህነት ላይ የከፈቱት ዘመቻ ውጤት በማስመዝገቡ የተገኘ እንደሆነም አብራርተዋል።

በድህነት ላይ የሚደረግ ትግል ተጠናክሮ በመቀጠሉ እየተመዘገበ ያለውን ውጤት ለመቀልበስ የሃገራችን ብሔራዊ ጥቅም ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት የተሰለፉትን ፀረ ስላም ሀይሎች መታገልም ለነገ የሚባል አይደለም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

የተመጀረውና የተመዘገበው ልማት በሃገሪቱ ቀጣይነት የሚኖረው ሰላም ሲሰፍን ነው፤ የሃገሪቱ መከላከያ ሰራዊት የሃገሪቱን ሰላም ከማስጠበቅ አልፎ የሌሎች ሃገሮችን ሰላም በማስጠበቅ የላቀ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑንም ተናግረዋል።

9ኛው የሰንደቅ አላማ ቀን በትምህርት ቤቶች፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶችና ቆንስላዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በመስቀል ነው እየተከበረ የሚገኘው።

የዘንድሮው በዓል እንደወትሮው በስታዲየሞች እና በሰልፍ ሳይሆን፤ በእለቱ 5 ሰዓት ላይ በትምህርት ቤቶች፣ በመንግስት መስርያ ቤቶች እና ቆንስላዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በመስቀል እንደሚከበር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱለ ገመዳ መግለፃቸው ይታወሳል።

ይህ የሆነውም በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመታወጁ ነው።

የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነት መገለጫ፣ በብዝኃነት ላይ የተመሰረተ አንድነታችን አርማ ነው” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው።