Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ተሃድሶውን መሰረት አድርጎ የተሰራ የፌደራል መንግስት ካቢኔ አዲሱ አደረጃጀት ነገ ይፋ ይሆናል፡-ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

ጥቅምት 21፡2009
ተሃድሶውን መሰረት አድርጎ የተሰራ የፌደራል መንግስት ካቢኔ አዲሱ አደረጃጀት ነገ ይፋ እንደሚሆን ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን አስታወቁ።
demeke-mokenen
ኢህአዴግ እያካሄደ ባለው ጥልቅ ተሃድሶ የነበሩ ችግሮችን መለየት እነርሱም በማያዳግም ሁኔታ መፍትሄ መስጠት ላይ ባተኮሩን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ገልፀዋል፡፡
በዚህ መርህ በመነሳቱ አራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች ጥልቅ ተሃድሶ በማድረግ የአመራር መልሶ ማደራጀት ስራዎች በፍጥነት እያከናወኑ መሆናቸውንም ነው አቶ ደመቀ የተናገሩት፡፡
በዚህ መልኩ ተሃድሶውን መሰረት አድርጎ የተሰራ የፌደራል መንግስት ካቢኔ አዲሱ አደረጃጀትም ነገ ይፋ ይሆናል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ሹመት የሚፈፀምላቸው የመንግስት ካቢኔዎች ለህዝቡ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ ታስቦ መመልመላቸውን ነው አቶ ደመቀ የገለፁት፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ድርጅቱ በህዝብ አደረጃጀት ወቅቱን የሚመጥን መሆኑንም አንስተዋል፡፡
አዲሱ ካቢኔ የህዝብን ችግር በሚፈታ በተለይም የወጣቶችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ሃላፊነት የተጣለበት ነው ብለዋል፡፡
የተሃድሶ ሂደቱ በካቢኔ ማዋቀር ብቻ የሚቆም ሳይሆን ህዝብን ባሳተፈ ንቅናቄ ችግሮችን ከመሰረቱ ለመፍታት የሚሰራ እንደሚሆንም ነው የገለፁት፡፡