Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በ85 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የመድሃኒት ፋብሪካ ለመገንባት በዱከም የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

medical-factory
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሳንሸንግ ኢትዮጵያ ፋርማሲውቲካል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የተባለ የቻይና ኩባንያ በዱከም የመድሃኒት ፋብሪካ ሊገነባ ነው።

85 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የሚደረግበትን ይህን ፋብሪካ ለመገንባት ትናንት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ፋብሪካው ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ በዓመት 10 ቢሊየን ኪኒን እና 5 ቢሊየን እንክብል የማምረት አቅም አለው።

ፋብሪካው 300 ለሚሆኑ የአከባቢው ነዋሪዎችም የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር መብራቱ መለስ በስነ ስርዓቱ ላይ ኩባንያው ኢትዮጵያ ሰፊ የማህበረ ኢኮኖሚ ሽግግር እያደረገች ባለችበት ወቅት መምጣቱ ትክክለኛ ጊዜ ነው ብለዋል።

የአገር ውስጥ መድሃኒት የማምረት አቅምንም የእንደሚያሳድግ ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና ኢምባሲ የኢኮኖሚ እና ንግድ አማካሪ ልዩ ዩ በበኩላቸው ፋብሪካው የኢትዮጵያን መድሃኒት የማምረት አቅም ከማሳደግ ባለፈ ለአከባቢው ነዋሪ ተጨባጭ ጥቅም የሚያመጣ እንደሆነ ተናግረዋል።