Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ ምክንያት የ52 ሰዎች ህይወት ማለፉን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ገለፀ

erecha
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ ምክንያት የ52 ሰዎች ህይወት ማለፉን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ገለፀ።
የክልሉ መንግስት በዛሬው የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ የተከሰተውን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፥ “የክልሉ ህዝብ በዓሉን ለአለም አምረው እና ደምቀው በሚገባ ለማሳየት ከፍተኛ ጉጉት እና ምኞት የነበረው በመሆኑም በዚሁ ምክንያት በተለያዩ የክልላችን አካባቢዎች እና የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም የተለያዩ አለምአቀፍ እንግዶች የታደሙበት ሆኖ ሳለ ለባህላችን እና ለህዝባችን ምንም ደንታ የሌላቸው ኃይሎች በጠነሰሱት እኩይ ሴራ ምክንያት ሁከት እና ብጥብጥ ተፈጥሯል” ብሏል።
መንግስት ከፍተኛ ትግስት እና ጥንቃቄ ያደረገ ማድረጉን የገለፀው መግለጫው “የጥፋት ኃይሎች ስርዓቱ በአግባቡ እንዳይፈፀም ለህዝቡ እና ለአባገዳዎች ምንም አይነት እክብሮት ሳይሰጡ እንዲስተጓጎል አድርገውታል” ነው ያለው።
በዚህም በተፈጠረ መገፋፋት እና መረጋገጥ ምክንያት ዜጎች ውድ ህይወት መጥፋቱን አስታውቋል።
ይህም ሁኔታ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ምክንያት እንጂ በአንዳንድ ማህበራዊ ድረ-ገፆች እንደሚሰራጨው የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ምክንያት እንዳልሆነ በአካባቢው የተገኘው ህዝባች ምስክር መሆኑንም ነው የገለፀው።
በጥፋት ኃይሎች እኩይ ተግባር ህይወታቸውን ላጡት ዜጎች መንግስት ጥልቅ ሀዘን ይሰመዋል ያለው የክልሉ መንግስት፥ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው የክልሉ ህዝቦች መፅናናትን ተመኝቷል።
ከተጎጂ ቤተሰቦች ጎን በመቆምም አስፋላጊ ሆኖ የተገኘውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
መንግስት እንደትላንቱ ሁሉ ከህዝቡ ጋር በመሆን ዛሬም የገዳ ስርዓት በአለም ዘንድ እንዲታወቅ ለማድረግ የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ብሏል።
ይህንን የህዝቡን ጥቅም የሚጎዳ እና ከባህል ውጪ የሆነ አሳዛኝ ድርጊት ህዝቡ አምርሮ እንዲያወግዝም ክልላዊ መንግስቱ ጥሪ አቅርቧል።
related news: የኢሬቻ በዓል አንዳንድ ወገኖች በፈጠሩት ሁከት ሳይከበር ቀረ
achare-in-oromia-distruption

የኢሬቻ በዓልን ባህላዊ አከባበር ጠብቆ ለማክበር የኦሮሞ ህዝብ አባገዳዎችና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያደረጉት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት በሁከት ፈጣሪ ኃይሎች ምክንያት መስተጓጎሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በበዓሉ አከባበር ላይ አባገዳዎች በዓሉን በሰላም እየመሩ እያለ ለሁከት አስቀድመው የተዘጋጁ ኃይሎች ሁከትና ግርግር በማስነሳታቸው በዓሉ እንደተፈለገው ሳይጠናቀቅ ቀርቷል።
አንዳንድ ሁከት ፈጣሪ ወገኖች መድረኩን በመያዝ እና የድምጽ ማውጊያ በመቀማት ከበዓሉ ባህላዊ የአከባበር እሴቶች ውጪ ባፈነገጠ መልኩ የሌሎችን የፖለቲካ መልእክቶች ለማስተላለፍ ሲሞክሩ ተስተውሏል።

ሁከት ፈጣሪዎቹ ባስነሱት ሁከትም በተፈጠረ ግርግር በመረጋገጥ የሰው ህይወት መጥፋቱን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
የኢፌዴሪ መንግስት የገዳ ስርዓትን በዩኔስኮ ለማስመዝገብና የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እያለ የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በዚህ መልክ በመስተጓጎሉና የሰው ህይወት በመጥፋቱ ከፍተኛ ሃዘን እንደተሰማው ገልጿል።
በሁከቱ በፈጠረው ግርግርና መረጋገጥ ህይወት መጥፋቱ የታወቀ ሲሆን በርካታ ተጎጂዎች ወደህክምና ቦታ መወሰዳቸውንም የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የኢፌዴሪ መንግስት ዝርዝር መረጃውን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ የገለጸ ሲሆን፥ ለዚህ ጥፋት ተጠያቂ የሆኑ አካላትንም ለህግ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።

የኢፌድሪ ህ.ተ.ም.ቤት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በዛሬው እለት በዜጎቻችን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ድርጊት አስመልክቶ ከነገ ጠዋት 12 ሰአት ጀምሮ የ3 ቀናት የሃዘን ቀን አውጇል፡፡ Source Addiss Abeba EPRDF facebook page .

nmdoromia-death

Reuters : read more read more on reuters

By Aaron Maasho
ADDIS ABABA (Reuters) – More than 50 people were killed in a stampede in Ethiopia’s Oromiya region that was triggered when police used teargas and shot in the air on Sunday to disperse anti-government protesters at a religious festival.
The state broadcaster put the death toll at 52, citing regional officials. The opposition also said at least 50 people were killed at the annual festival where some people had chanted slogans against the government and waved a rebel group’s flag.
Sporadic protests have erupted in Oromiya in the last two years, initially sparked by a land row but increasingly turning more broadly against the government. Since late 2015, scores of protesters have been killed in clashes with police.
The developments highlight tensions in the country where the government has delivered stellar economic growth rates but faced criticism from opponents and rights groups that it has reduced political freedoms.
Thousands of people had gathered for the annual Irreecha festival of thanksgiving in the town of Bishoftu, about 40 km (25 miles) south of the capital Addis Ababa.
Crowds chanted “We need freedom” and “We need justice”, preventing community elders, deemed close to the government, from delivering their speeches.
Some protesters waved the red, green and yellow flag of the Oromo Liberation Front, a rebel group branded a terrorist organization by the government, witnesses said.
When police fired teargas and guns into the air, crowds fled and created a stampede, some of them plunging into a deep ditch.
The witnesses said they saw people dragging out a dozen or more victims, showing no obvious sign of life. Half a dozen people, also motionless, were seen being taken by pick-up truck to a hospital, one witness said.
“As a result of the chaos, lives were lost and several of the injured were taken to hospital,” the government communications office said in a statement, without giving figures. “Those responsible will face justice.”
Merera Gudina, chairman of the opposition Oromo Federalist Congress, told Reuters at least 50 people had died, based on details provided by families of the victims.
He said the government tried to use the event to show Oromiya was calm. “But residents still protested,” he said.
The government blames rebel groups and dissidents abroad for stirring up the protests and provoking violence. It dismisses charges that it clamps down on free speech or on its opponents.
Protesters had chanted slogans against the Oromo People’s Democratic Organisation, one of the four regional parties that make up the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front, which has ruled the country for quarter of a century.
In a 2015 parliamentary election, opposition parties failed to win a single seat – down from just one in the previous parliament. Opponents accused the government of rigging the vote, a charge government officials dismissed.
Protests in Oromiya province initially flared in 2014 over a development plan for the capital that would have expanded its boundaries, a move seen as threatening farmland.
Scores have been killed since late in 2015 and this year as protests gathered pace, although the government shelved the boundary plan earlier this year.