Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የተከለከሉ ነገሮች ተፈፅመው ሲገኙ ስለሚወዱ እርምጃዎች

state-of-emergency-not-to-do-list
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እርምጃ ለመውሰድ ስልጣን ስላለው ሰው በተደነገገበት የመመሪያው ክፍል፤ የህግ አስከባሪዎች የመመሪያውን ድንጋጌ ተላልፈው በተገኙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን እርምጃዎች መውሰድ እንደሚችሉ ተመላክቷል።
ክልከላዎች ሲጣሱ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ፤ በመመሪያው የተከለከሉ ተግባራት ተፈፅመው ሲገኙ፤
1. ህግ አስከባሪዎች ተጠርጣሪዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል ይችላሉ፤
2 አዋጁ ተፈፃሚነቱ እስከሚያበቃበት ድረስ ኮማንድ ፖስቱ በሚወስነው ቦታ እንዲቆዩ የማድረግ፤
3 ተገቢውን የተሃድሶ ትምህርት በመስጠት የሚለቀቀውን እንዲለቀቅ፣ ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርበውን ደግሞ እንዲቀርብ ማደረግ
4 ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በማንኛውም ስአት ብርበራ የማድርግ፤ የአካባቢውን ህዘብ እና ፖሊስ በማሳተፍ ማንኛውንም ወንጀል የተፈፀመበት ወይም ሊፈፀምበት የሚችል ንብረት መያዝ፤ወይም ንበረቱ እንዲጠበቅ ማደረግ
5 በማንኛውም ሬድዮ ቴሌቭዠን ድምፅ፣ ምስል ፎቶ ግራፍ፣ ቲያትር እና ፊልም የሚተላለፉ መልእክቶችን መቆጣጠር እና መገደብ
6 የተዘረፉ ንብረቶችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በመፈተሽ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ማድረግ
7 በትምህርት ተቋማት ሁከት እና ረብሻ ተሳትፎ በሚያደርጉ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ላይ ህጋዊ እርምት መውሰድ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለተቋማቱ ትእዛዝ መስጠት
8 ማንኛውም የህዝብን ሰላም እና ፀጥታ ሊያደፈርሱ ይችላሉ ወይም ለጉዳት ተጋላጭ ይሆናሉ ተብለው የሚጠረጠሩ እና የሚታሰቡ ሰዎችን እንዲሁም ቡድኖችን ወደ ተወሰነ አካባቢ እንደይገቡ፣ እንዳይገኙ ወይም በተወሰነ አካባቢ ብቻ እንዲቆዩ ማድረግን ጨምሮ አግባብነት ያለቸውን እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል።
ራስን ለመከላከል በፀጥታ ሀይልች ስለሚወሰድ እርምጃም መመሪያው ድንጋጌዎችን አስቀምጧል።
ህግ አስከባሪዎች እና በድርጅት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጦር መሳሪያ ወይም በስለት ህይወታቸውን እና ንብረተቻውን አደጋ ላይ የሚጥል ጥቃት በተሰነዘረ ጊዜ ራሳቸውን ለመከላከል የሚያስችላቸውን እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ።
በትምህርት ተቋማት የመግባት ስልጣንም በመመሪያው ስንጋጌ ወጥቶለታል። መመሪያው እንደሚለው በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝ እና ችግሩን ለማስቆም የህግ አስከባሪ አካላት በተቋማቱ ውስውጥ በመግባት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይችላሉ።
በሌሎች የመንግስት እና የግል ተቋማት አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝ እና ሰላም እና ፀጥታ ለማረጋገጥ የህግ አስከባሪ አካላት እና ባልደረቦች በተቋማቱ ውስጥ ለመግባት እና አስፈላጊ ከሆነ ለማቆየት ይችላሉ።
ተሃድሶ እና ፍርድ ቤት ማቅረብን በተመለከተም መመሪያው ይህንን ይላል፤ 
በህግ መሰረት በኮማንድ ፖስቱ የሚደረግ የተሃድሶ እርምጃዎች እንደሚኖሩ በተጠቀሰበት የአዋጁ ድንጋጌ፤ ኮማንድ ፖስቱ ለፍርድ መቅረብ ያለበትን እንዲቀርብ ያደርጋል፤
ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በተፈፀሙ የሁከት እና የነውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ በቡድን ወይም በግል የተሳተፈ
የጦር መሳሪያ ሳይዝ የመንግስትም ሆነ የግለሰን ንብረት የዘረፈ እና በአቅራቢያው ለሚገኝ ፀጥታ አስከባሪ ሃይል የዘረፈውን መሳሪያ እና ንብረት፤ ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰ እና እጁን የሰጠ ፤
ከዚህ በፊት ለህገ ወጥ ተግባራት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ፣ወረቀት በመበተን፣ አድማ በማድርግ የተሳተፈ እና ያነሰሳ፣ ሰው የገደለ፣ማንኛውንም ንብረት ያቃጠለ፣ማንኛውንም ወንጀል የፈፀመ ስው፤
ይህ መመሪያ ከወጣ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የመለሰ እና እጁን ከሰጠ እንደ የወንጀል ተሳትፎው ቀላል እና ከባድነት ዋና ፈፃሚ እና አባሪ ተባባሪ መሆኑ ታይቶ፣ በኮማንድ ፖስቱ የተሃድሶ ትምህርት ተሰጥቶት እንዲለቀቅ ይደረጋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ “በተወሰኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እንዳይፈጸሙ የተከለከሉ ተግባራት” ተፈጻሚ የሚሆኑባቸው ስፍራዎች ይፋ ተደርገዋል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጠ በተወሰኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እንዳይፈጸሙ የተከለከሉ ተግባራት ተፈጻሚ የሞሆኑባቸው ስፍራዎች ኮማንድ ፖስቱ ይፋ አድርጓል።
እነዚህም ከድንበሮች 50 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ ያሉ ስፍራዎች ቀይ ዞን ተብሎ በመመሪያው ላይ ተለይተዋል።
በነዚህ ስፍራዎች የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ፣በልማት አውታሮች እና በመሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መሰንዘር እና ሁከትን ለማስቆም እና አደጋን ለመከላከል የሚደረግ እንቅስቃሴን ማወክ የሚሉት ክልከላዎች ተግባራዊ ይሆናሉ።
እንዲሁም በዋና ዋና የሀገሪቱ መንገዶች ማለትም፥ ከአዲስ አበባ ጅቡቲ፣ ከአዲስ አበባ ሻሸመኔ ዶሎ፣ ከአዲስ አበባ ሀረር፣ ከአዲስ አበባ አሶሳ፣ ከአዲስ አበባ ጋምቤላ፣ ከአዲስ አበባ ገብረ ጉራቻ፣ ከጎንደር መተማ፣ ከጎንደር ሁመራ፣ ከአዲስ አበባ ሻሸመኔ ሞያሌ 25 ሜትር ወደ ቀኝ እና 25 ሜትር ወደ ግራ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ፣ በልማት አውታሮች እና በመሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መሰንዘር እና ሁከትን ለማስቆም እና አደጋን ለመከላከል የመኒደረግ እንቅስቃሴን ማወክ አይቻልም።
ቀይ ዞን ተብለው የተለዩት አካባቢዎች በሀገሪቱ የተወሰኑ አካባቢዎች እንዳይፈጸሙ የተከለከሉ ተግባራት የሚተገበሩባቸው ናቸው።