Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በሰበታ ሁከት ፈጣሪዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ40 ሺህ በላይ ሰራተኛን የያዙ 11 ፋብሪካዎችና 60 ተሽከርካሪዎች ወድመዋል

sebta-destruction
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 26 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰበታ ባለፉት ቀናት ሁከት ፈጣሪዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ40 ሺህ በላይ ሰራተኛ የያዙ 11 ፋብሪካዎችና 60 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል።
ዛሬ በአከባቢው ቅኝቱን ያደረገው ሪፖርተራችን ሳይገን ዲማ፣ ቱቱ ጨርቃጨርቅ፣ አባቦ ጉና፣ አባቦ ሀይላንድ እና ሮቶ ፕላስቲክን ጨምሮ በጠቅላላው 11 ፋብሪካዎች መቃጠላቸውን ታዝቧል።
ፋብሪካዎቹ ከ40 ሺህ በላይ ሰራተኛን የያዙ ሲሆን፥ አብዛኛዎቹም የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸው ነው ፖሊስ የገለፀው።
ንብረትን በግፍ የማውደም ተግባሩ ቀጥሎ 62 የህዝብና የተቋማት ተሽከርካሪዎችን በከፊልና በሙሉ አውድመዋል።
ሪፖርተራችን በስፍራው ተገኝቶ ያነጋገራቸው የዓይን እማኞች ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩ ሰዎች በአከባቢው ብዙም የማይታወቁና ነዳጅና ጎማን ጨምሮ እንጨት በመያዝ ድርጊቱን ሲፈፅሙ እንደነበር እንዲሁም የሚንቀሳቀሱትም በተሽከርካሪ መሆኑን ነው የገለፁት።
ግለሰቦቹ ዛሬ ቀትር አጋማሽ ድረስ የንግድ ቤቶች እንዳይከፈቱና ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ሲሯሯጡም ነበር።
ከወለቴ ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የንግድ ቤቶች መዘጋታቸውንና የሰዎች እንቅስቃሴም ከወትሮ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ታዝበናል።
የጸጥታ ሀይሎችም በመስመሩ በመመላለስ የጽጥታውን ሁኔታ ሲቃኙም ነው የተመለከትነው።
የአከባቢው እንቅስቃሴ የተቀዛቀዘው ከማክሰኞ ጀምሮ መሆኑንም ነው ነዋሪዎች የገለፁልን።
የሰበታ ከተማ አስተዳደር አሁን ላይ አስፈላጊው የጥበቃ ስራ ስለተሰራ ከነገ ጀምሮ ነዋሪውም ሆነ የንግዱ ማህበረሰብ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴ መመለስ ይችላል ብሏል።
sebeta-1

sebeta-2

sebeta-3

sebeta-4

sebeta-5

sebeta-6

sebeta-7

sebeta-8

sebeta-9