Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ከኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

opdo-mark

የኦህዴድ መእከላዊ ኮሚቴ ከመሥከረም 4-10/2009 ዓ.ም በአዳማ ባካሄደው ጥልቅ የተሀድሶ ግምገማ የድርጅቱን የ15 ዓመታት የስኬት ጉዞ እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በመገምገም የወደፊት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

ባለፉትአስራ አምስት አመታት በኋላ ቀርነት እና በድህነት ላይ በተካሄደው ዘመቻ በክልሉ የገጠርና የከተማ አከባቢ ብሩህ ተስፋ እንዲለመልም ማድረግ ተችሏል ብሏል፡፡
መግለጫው በግብርናና በገጠር ልማት እስትራቴጂ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የግብርና ኤክስቴሽን በማስፋፋትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማሻሻል፣ የህዝቡ ጠላት የሆነ ድህነትን በመቀነስ አርሶአደሩ ኑሮውን አንዲያሻሽል የተኬደው ርቀት አብይ ማሳያ መሆኑን ገልጾ ለዚህ ምስክሩ ተጠቃሚ መሆን የቻለው የኦሮሞ ህዝብ ነው ብሏል፡፡

ድርጅቱ በመግለጫው ለተገኘው ስኬት ለአርሶ እና አርብቶ አደሩ እንዲሁም የግብርና በለሙያዎችን አመስግኗል፡፡
የአርብቶአደሩን አከባቢ ልማት በተመለከተ የእርብቶ አደሩን ሕይዎት ለማሻሻል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አርብቶ አደሩ የመሠረት ልማት አውታሮች ፣ የትመህርት ፣ የጤና ፣ የመጠጥ ውኃ፣ የእንስሳት የገቢያ ትስስር ፣የእስሳቶች የጤናና የኤክስቴንሸን አገልግሎት እንዲያገኝ በተደረገው ጥረትም ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧልም ብሏል፡፡

ገጠሩን የኦሮሚያ ክልል ከኋላ ቀርነት ለማላቀቅ በሰው ሀብት ልማት ላይ በተሰራው ስራ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀዬያቸው ሳይርቁ የትህምርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተሰጡ ትኩረትም የተገኘው ውጤት አኩሪ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ኦህዴድም ይህንን ድል ለማስመዝገብ ከባለእርሻ አካላት፣ ጋር በቅንጅት መስራት በማቻሉ ስለሆነ ለተገኘው ውጤት ላቅ ያለ ምስጋና አለው ብሏል፡፡

ገጠሩ የኦሮሚያ አከባቢ ከተለያዩ በሽታዎች አስቀድሞ ለመከላከል በተደረገው ጥረት ትልቅ ለውጥ ከማምጣት ባሻገር የምዕተ አመቱን የልማት ግቦች እንዲሳኩ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በተለይ ለእናቶችና ህጻናት ጤና አጠባበቅ ፣ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር በተዘረጋው አሰራር የተሸለ ውጤት ማምጣት ተችሏል ብሏል መግለጫው፡፡

በሁሉም ረገድ የሚከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች መሠረት አንዲኖራቸውና በመሠረት ለማት ዝርጋታ የመንገድ ፣ የመጠጥ ወኃ፣ የኤሌክትሪካል ኃይል አቅርቦት የቴሌኮም መስፋፋት በአንድ ክፈለ ዘመን ተሰርቶ በማይታወቅ መልኩ መስፋፋታቸውን ገልጾ የፕሮጀክቶች መጓተት በተደራሽነት እና ጥራት በኩል ውስንነቶች ያሉ ቢሆንም የተከናወነው ተግባር በየትኛው መስፈርት የሀገርቱን የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ታሪክ የቀየረ መሆኑን አመልክቷል፡፡

በከተማ ልማት እና እንዱስትሪ ዘርፍ የከተማና የገጠሩ ነዋሪዎችን በማስተሳሰር፣ ዘላቂ ልማት እንዲኖር ፣ ከተማን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እና የእንዱስትሪ መዕከል እንዲሆን ውጤታማ የሆኑ ትላለቅ ስራ ተስርቷል፡፡ በተለይ በከተማው በስፋት የሚስተዋለውን ስራ አጥነትና ድህነትን በመናድ የስራ በህል እንዲጎለብት ስራ የማይነቅ ዜጋ ለማፍራት የቁጠባ ባህል ለማደበር የጥቃቅን አነስተኛ እንተርፕራይዝ ልማት ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት የተመዘገበ ነው፡፡

በዚህም በራሱ የሚተማመን ሰርቶ በድካሙ ሀብት የሚያፈራና ለልማታዊ በለሀብትነት መሠረት የሚሆኑ ዜጎችን ለማፈራት በተከናወነው ተግባር ተስፋ ሰጪ ውጤት የተመዘገበ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡በሚዬን የሚቆጠሩ ሴቶች እና ወጣቶችም የዚህ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት እድገትና ፍታሃዊ ነት በትክክለኛ ተሰፋ ሰጪ አቅጣጫ ላይ መሆኑ ተርጋግጧል ፡፡ለዚህ ስኬትም ድርጅቱ ለበለድርሻ አካላት በሙሉ ትልቅ አድናቆት አንዳለው ይገልፃል ፡፡

በገዢ መደቦች ተገፍቶና ተቀብሮ የነበረወ የኦሮሞ ህዝብ ታሪክና ባህል ኦሀዴድ በከፈለው አኩሪ መሰዋትናት ባለፉት 15 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ አንገት ቀና ያስባለ ድል ማጎነጻፍ መቻሉን ሲገልፅ ለዘላለም በኩራት የሚኖርበት ታሪክ በድርጅቱ የተገኘ ድል መሆኑ ልሰመርበት ይገባል፡፡

በዚህም አፋን ኦሮሞ የምንግስት የሥራ ቋንቋ የጥናትና ምርምር፣የሣይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የሚዲያ ቋንቋ ማደረግ መቻል ትልቁ ማሳያ ነው፡፡የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ተደብቆ ከነበረበት ይፋ አንዲወጣ በአፈ ታሪክ ሳይሆን በፅሁፍ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ምቹ መደላደልም ተፈጥሯል፡፡

ከዚህ ባሻገር ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ቁርኝት ያለቸውና ልዩ ትርጉም ያለቸውን ታሪካዊ ስፍራዎችን ልዩ ትኩረት ለመስጠትና በማልማት ድርጅቱ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ታሪካዊ ሃውልት ማቆም ችሏል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ለታሪኩ ቀጣይነት የኦሮሞ አገር ሽማግሌዎች ምሁራንና የድሉ ባለቤት የሆነው አዲሱ ትውልድ ትልቅ ደስታና ስኬት ነው ብሎ ያማናል፡፡

ኦህዴድ ለሌሎችም ምሳሌ የሚሆንና አዲስ ካስመዘገባቸው ታሪኮች ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የክልሉ ሚዲያ በማቋቋም የኦሮሞን አንድነት የኦሮሞን ታሪክና ቋንቋን በማሳደግ ህዝቡ ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኝ ከመላው ሀገሪቱ ጋር እንዲገናኝና ከአለምጋር አንዲተሳሰር ህዝቡን ለማህበራዊና ልማት ስራዎች ተነሳሽነት እንዲኖረው የልምድ ልውውጥ እንዲያደርግ ልማታዊ ተልዕኮ ያለውን ሚዲያ መስርቶ መስራት መቻል ትልቅ ስኬት መሆኑም ሊታወቅ ይገባል፡፡ለዚህ ትልቅ ድል አስታዋዕፆ ለበረከቱ የሚዲያና ኮሙኒኬሸን በለሙያዎች ኦህዴድ ትልቅ ክብር እንዳለው ይገልፃል፡፡

አህዴድ የስራውን ስኬት ሁሌም ሲገመግም ያለፈውን የስራ መነሻና ባስመዘገበው ውጤት ተኩራርቶ እራሱን ለማመፃደቅ ሳይሆን ውጤቱቹ ያላቸው ትርጉም እና ሚስጥር ለወደፊት ትግሉ ያላቸውን አስታዋዕፆ ከግምት ለማስገባት ከገጠሙ ወስንነቶችን ተምህር በመውሰድ ለቀጣይ መዕራፍ እራሱን ለማዘጋጅት ባህሉ መሆኑንም ያስገነዝባል፡፡መቼም ቢሆን የድሎቻችንን መነሻ ስንገመግም ትክክለኛ አቅጣጫ እና ግልፅ በመሆን መጀመሪያውና መጨረሻው የህዝቡን ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይዘን ቁርጠኛ እና በባለቤትናት በመታገል መስዋዕት መሆን የሚችል አባል አፍርተንና በዲሞክራሲያዊ መርህና ባህል በየጊዜው ችግሮችን ለይቶ ለማስተካካል ዝግጁ በመሆን ጭምር የሚያገጥመንን እንቅፋት በሙሉ በጊዜ ማስተካከል መሆኑን ተርድተናል፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ የልማትና የዲሞክራሲ አቅጣጫውን የራሱ አድርጎ የድርጅቱን ባህሪ በመረዳት በጥንካሬም ሆን በድክመታችን ጊዜ አንደልጆቹ በመገፀፅና በመምከር አሳድጎና ስልጣኑን በመስጠት መቼም ቢሆን ጥቅሙ እንዲከበርለት በድርጅቱ ላይ እምነቱን በመጣልና ተስፋ በማድረግ ኃላፊነቱን ለሰጠው ህዝብ ድርጅቱ ሙሉ እመነት አለው፡፡ላለፉት 15 ዓመታት ባከሄድነው ትግል ያጋጠሙን ችግሮች በስራ ሂደት ያገጠሙ ችግሮች እንጂ የአቅጣጫ ችግር ያለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

ከዚህ ችግር በመማርና በማስተካከል የህዳሴውን ምዕራፍ በድል መሠረት ለማስያዝ ስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡ዋነኛው ችግሮች ናቸው ብለን ከለየናቸው መካከል የህዝባዊ ወገኝትነት ላይ ያለ አመለካከትና አብዮታዊ ዲሞክራሲ መሠረት በማድረግ በየደረጃ እያደገ የመጣው ከራስ ወዳድነት የተነሳ ስልጣን የህዝብን ማገልገያ መሣሪያ መሆኑን በመዘንጋት ከህዝብ በፊት እራስን መለወጥ የህዝብ አገልግሎት የተጓደለ በመምጣቱ በአስቸኳይ እነዚህን ችግሮች በማስተካከል ወደ ህዝባችን ልንመለስ ይገባል በሚል አቋም የትግላችንን ቃል እናድሳለን፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ያለቡን ድክመቶችና ያስመዘገብናቸው ድሎች በማመዛዘን እውቅና በመስጠት ያሉትን ችግሮችን ጊዜ ሳናባክን እንድንቀርፍለት እንደሚሻ እንገነዘባልን፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረንን ህዝባዊ ወገኝትነት ስናጓድል ቅሬታና ኩርፊያ አንዳለው በተለየ ሁኔታ ስላሳየ የህዝቡን ቅሬታ ለመቅረፍ ለመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን በነቃ የህዝቡ ተሳትፎ እንደምንመልሰው ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡በሌላ በኩል የመልካም አስተዳደር ችግሮችና በገጠርና በከተማ ያለው የስራ አጥነት ችግር ለመቀርፍ በሁሉት አቅጣጫ ተመልክተናል የመጀመሪያ እየጨመረ የመጣው የህዝቡ የመለወጥና የመልማት ፍላጎት ካጋጠመን የማስፈጸም አቅም ወስንነት በሚፈለገው መጠን ሟሟላት አልተቻለም ፡፡ በዚህም ህዝቡ ቅሬታ ቢኖረውም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር በኛ ትግልና የህዝቡ ታሳትፎ ችግሮችን እንደምንቀርፍ በመገንዘብ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቀን በከፍተኛ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

በዉስጥ አፈፃፀም ችግሮች ለጋጠመው የመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝባችንን በክብር ይቅርታ ጠይቀን በከፍተኛ የዉስጥ ትግል እና የሕዝቡ ድጋፍ ሠርተን ሕዝቡን ለመካስ ቃል እንገባለን፡፡
በዉስጥ ችግራችንና እንከኖቻችን የተነሳ የገጠሙ ችግሮችን በመጠቀም በክልሉ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ባናፈሱት አሉባልታ የፀጥታ ችግር ምክኒያት ለጠፋዉ የሰዉ ሕይወት እና ንብረት ዉዱመት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን የጥፋት ሃይሎች ስረዓቱን ከመሠረቱ ለመናድና ድሎቻችንን ወደ ኋላ ለመመለስ ያደረጉት መፍጨርጨር ባለበት ቦታ እንዲቆምና ችግሮቻችንን እንደ ተለመደዉ በዉይይት መፍታት እንዳለብን ለህዝባችን ጥሪ እናቀርባለን::

የጥፋት ሀይሎች አገርንና ስራዕቱን ለመናድ ያላቸዉን ተልዕኮ እንደተለመደዉ ትግሉ የሚጠይቀዉ መስዋዕትነት በመክፈል የምንታገል ሲሆን ለዚሁ የተለመደዉን የኦሮሞ ሕዝብ ድገፍ እንጠይቃለን ፡፡
የፀረ-ሰላም ሃይሎችም በአቋራጭ በብጥብጥ ስልጣን ለመያዝ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መቼም ሊሳካ እንደማይችል ተረድተዉ ከአሸባሪነትና ብጥብጥ ስራቸዉ እንደታቀቡ በድጋሚ ማሣሠብ እንወዳለን ፡፡
1ኛ ድርጅታችን ከየትኛዉም ዉጫዊ ችግር በማስቀደም በመጀመሪያ ዉስጣዊ ችግሮቹን በጥልቀት በመመርመርና በማጥራት ድርጅታችንን በማጠናከርና ወደ ሕዝባዊ ወገንተኝነት በመመለስ ትግሉን በማቀጣጠለል ለሮሞ ሕብብ ጥቅምና መብት ልክ እደትላንቱ በቆራጥነት ለመተገል ዝግጁ መሆናችችንን እናረጋግጣለን፡፡

2ኛ ድርጅታን ኦህዴድ ስልጣን የህብረተሰባችንን ሁንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጫ መሳሪያ መሆኑን ከመገንዘቡ የተነሳ የህዳሴያችንን ጉዜ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲያስችልን ለህዘቡ ያለውን ወገንተኝነት እራስ ላይ አስከመወሰን ድረስ ለመግለፅ የድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው በራሳቸው ፍቃድ ለመውረድ ለማዕከላዊ ኮሚቴው ጥቃያቄ በማቅረብ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ለቀመንበር ያቀረቡትን ጥያቄ ማዕከላዊ ኮሜቴው ውሳኔያቸውን በታላቅ አፅንዖት አይቶ በመወሰንና በአመራርነታቸው የነበራቸውን ተሳትፎ ግምት ውስጥ በማስገባት አንድ እርከን ዝቅ በማድረግ የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡

በምትካቸውም አዲስ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ተተክቷል፡፡
3ኛ በተጨማሪ በአመራርነታችን ክፍተት የመጡ ችግሮችን በጥልቀት በመመርመር የድርጅቱንና የመንግስትን ጠንካራ መዋቅር በማረጋገጥ የትግሉ ምዕራፍ የሚጠይቀውን አመራርነት ለመስጠት የህብረተሰባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዝግጁነታችንን እንገልጻለን፡፡

4ኛ የህበረተሳባችንን የእለት ተእለት ኑሮ ጠፍንጎ የያዙ የመለካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት የችግሮቹን ምንነት በየደረጃው ለመፍታት ህበረተሰቡን ባሰተፈ መልኩ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል፡፡የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ድርጊትን ያለምንም ምህረት ድል በማድረግ ለህዳሴያችን ጉዞ ስኬት እልህ አስጨራሽ ትግል እናደርጋልን፡፡ለዚህም የእናንተን የተለመደውን ርብርብ እንሻለን፡፡

5ኛ የህዳሴያችንን ጉዞ በአንድ ሌሊት ከዳር ማድረስ አዳጋች መሆኑ እውን ነው፡፡የህዳሴው ጉዞ በሂደትና ቀጣይነት ባለው መልኩ ከተሰበበት የሚደርስ መሆኑ ይታመናል፡፡በመሆኑም በጥልቀት ለመታደስ በአመራሩ ፣በሰፊው አባላትና በህዝቡ ዘንድ ደርሶ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ያላንዳች እርፍት እንደምንሳራና ለህዳሴያን ስኬት የሁላችን ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ዛሬም እንደትናንቱ በእኔነት ስሜት እንድትረባረቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

6ኛ -አንድነታችን በማጠናከር ተጠቃሚነታችንን እንደምናረጋግጠው ሁሉ ከአገራችንና ጎረቤቶች ሕዝቦች ጋር በወንድማማችና መቻቻል ቅርርብ በመከባበር ልክ እንደ ትናንቱ ዛሬም ክንዳችንን አጠናክረን በድሕነትና ኋላ ቀርነት ላይ የጀመርነዉን ትግል አጠናክረን በማስቀጠል ለአገርቱ የሕዳሴ ጉዞ ስኬት የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን፡፡

7ኛ፡- የሕዝቡንና የዴሞክራሲ ተቋማትን ግንባታና አደራጃጀት በማጠንከር በሁሉም ዘርፍ የሕዝቡን ተሣትፎ በተደራጁ መልኩ በማረጋገጥ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታውን መሬት በማስያዝ እያሣደግን ለመሔድ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ለመስራ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡

8ኛ አገራችን በደረሰችበትን አገራዊ እድገት መሠረት የሕዝብ ልማት ስራችን በከፍተኛ ሁኔታ እያደረገ መቷል፡፡ይሁን እንጅ በክላችን የተማረው ኃይልና ወጣቱ በሚፈለገው መልኩ ተጠቃሚ መሆን ባለመቻሉ ወጣቱና ቤተሠቦቻቸው ትክክለኛ ጥያቄ በመጠየቃቸው ድርጅታችን በከፍተኛ የተጠያቅነት መንፈስ እና ሙሉ እምነት በመቀበል ችግሩን ለመቅረፍ መስራት እንደጀመርነው በትኩረት በስፋት እንደምንሰራበት እና መሰረታዊ ለውጥ መምጣት እንደምንችል በሙሉ እምነት እንገልጿለን፡፡በዚሁ የክልላችን ወጣቶች የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡

9ኛ፡- ድርጅታችን ከሕዝባዊ ወገንተኝነቱ የተነሳ አርሶአደሩ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በተለይም በልማት ምክንያት ከመሬታቸው እንዲነሱ የተደረጉ አርሶአደሮችን ጉዳይ በጥልቀት በመመርመር ተጠቃሚነታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማረጋገጥ በጠንካራ አደረጃጀትና አሰራ በመደገፍ ከዚህ ቀደም በአፈፃተም ይታዩ የነበሩ ችግሮችን ከመሰረቱ በማጥፋት ተጠቃሚነታቸውን እናረጋግጣለን፡፡

10ኛ፡- በድንበር አካባ በተለያዩ ጊዜያት የሚያጋጥመውን ግጭት በልዩ ትኩረትና ቆራጥነት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካት ጋ በመሆን ለመፍታ የምንሰራ መሆኑን በመግለፅ ሕብረተሰባችን ችግሮች ሲያጋጥሙ በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ ለማፍታት ርብርብ ማድረግ እንዳለበት ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡

11ኛ፡- ሰላ ለሁሉም መሰረት መሆኑን ከሕብረተሰባችን በላይ የሚያውቅ አለ ብሎ መውሰድ አይቻል፣ም፡፡ ከምንም በላይ ያሉብብበ ችግሮች ትኩረት ሰጥቶ በማየት ለችግሩ እልባት ለመስጠት ብሎም ተጠቃሚ ለመሆን ወሳኙ ጉዳይ ሰላ ነው፡፡

ድርጅታችን ኦህዴድ ሁሌም ትልቁ ጠላታችን ድህነት ነው ብሎ ያምናል፡፡ ከዚህ በዘለለ በሰላማችንና ልማታችን ላይ እንቅፋት የሚሆኑት የጥፋት ኃይሎች ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል በመናድ ስልጣንን በአቋራ ለመያዝ ለሚፈልጉ ኃይሎች ሕብረተሰባችን እንደማይፈቅድላቸው በተጨባጭ አረጋግጧል፡፡ስለዚህ ሕብረተሰባችን በሁሉም ደረጃ ትልቅ መስዋዕትነት በመክፈል በግንባር ቀደምትነት የአካባቢውን ሰላ ለማስከበር ላደረገው ርብርብ ታላቅ ክብር እናቀርብላቸዋለን፡፡
ከዚህም በኋላ ለኑሯችን መሰረት የሆነው ሰላም እንዳይደፈርስ ሕብተሰባችን አሁን ያደረገውን ትልቅ ተሳትፎ ተጠናክሮ በመቀጠል የጀመርነው ልማታችን ከዳ እንዲደርስ ከሕብረተሰባችን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ለመስራ ያለንን ዝግጁነት በግለፅ አሁንም ለሕብረተሰባችን ዳግም ጥሪያን እናስተላልፋለን፡፡
12ኛ፡- የአካባቢያችንን ሰላም ማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ ሁ የሕግ የበላይነት መስፈንም ለዜጎቻን ኑሮ ትልቁ ዋስትና ነው፡፡ በመሆኑ ለዚሁ ስራ ስኬት የሰፊው ሕብረተሰባችን፤የፍትህ አካትና የፀጥታ አካት ድርሻ ወሳኝ ነው፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሁሉም ዜጋ ያንዳች ሥጋት የተጀመሩ የልማት፤የዴሞክራሲ ስርዓተር ግንባታ ስራዎችን ከለዳር ማድረስ እንዳለበት ጥሪያችንን እንቀርባለን፡፡

በመጨረሻ |የሕዳሴ ጉዞአችን እንዲሳካ በማድጉ ረገድ ከምንም በላይ መዋቅሮቻን በትልቅ ዝግጁነት እንዲተገብሩና እንዲያስተገብሩ እንዱሁም ሕብረተሰቡ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ተሳትፎውን ማጠናከር እንዳለበት ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የሕዳሴያችን ጉዞ እንዲሳካና የሕብረተሰባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እውን እንዲሆን ርብርብ ማድረግ እንዳለባችሁ ታላቅ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ
መስከረም 11/2009
አዳማ