Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ኢትዮጵያ በእኩልነትና በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ እንድነትን የሚያረጋግጥ ስርዓት ዘርግታለች- አቶ አባይ ፀሃዬ

Ethiopia realizes system guaranteeing democratic unity of people abay
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰላም እና መረጋጋት፣ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት የተሻላ የዴሞክራሲ ሰርዓት ግንባታ፣ የኢትዮጵያ ስም ሲነሳ አብረው የሚነሱ መገለጫዎቿ ሆነዋል።

ይህንን የሰማነው ባለፉት 25 አመታት በተሰሩ ስራዎች እና በመጡት ለውጦች ነው።

የእነዚህ አመታት መገለጫዎች ግን ይሄ ብቻ አይደለም የመልካም አስተዳር እጦት የወለደቻው ምሬቶችም ታይተውባቸዋል።

ዛሬ ከሩብ ምዕተ ዓመት በኃላ ኢትዮጵያውያን በህይወት መስዋትነት የተከሉት ስርዓት ምን ይዞላቸው መጣ።

በሚኒስትር ማእረግ የኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር ማእከል ዳይሬክተር አቶ አባይ ጽሃዬ የለውጡን ሁሉ መነሻ የእድገትን ሁሉ መሰረት የለውጦች ሁሉ ቁንጮ ይሉታል።

ኢትዮጰያ በትርምስ ውስጥ ባለው የአፍሪካ ቀንድ ያለች ሀገር ብትሆንም እንደ ህዝቦቿ ተግባቦት ግን በደፈረሰ ቀጠና ወስጥ ያለች ሰላማዊ ሀገር መሆኗን ያነሳሉ።

ይህ ሰላም የእድገት መሰረት ሆኗልና ኢትዮጵያም በሁለት አስርት አመታት ያሳካችው ሌላው ለውጥ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ነው።

አቶ አባይ ሀገሪቱ በመጀመሪያዎቹ 12 ዓመታት ያስመዘገበችው እድገት 5 ነጥብ 5 በመቶ እንደነበር ያስታውሳሉ።

“ከኢህአዴግ ተሃድሶ በኋላ ግን ኢትዮጵያ በየዓመቱ የ10 በመቶ አማካኝ እድገት እያስመዘገበች መጥታለች” ነው የሚሉት።

“እድገቱ የሰላም ጅምሩ እና የልማት ጅምሩ ተስፋ ሰጪ እና አበረታች ነው” የሚሉት አቶ አባይ ጽሃዬ፥ ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ እናደርሳታለን የሚያሰኝ ነውም ብለዋል።

ዛሬ ኢትዮጵያ የፈጣን እድገት ምሳሌ ከሆኑት ሀገራት አንዷ ቻይና በ1970ዎቹ በደረሰችበት ደረጃ ላይ መድረሷን የሚያነሱ የኢኮኖሚ ልሂቃን አሉ።

አቶ አባይ ከኢኮኖሚው ባሻገር በዴሞክራሲ ስርኣት ግንባታ ተመዘገበ የሚሉት የ25 አመት ውጤትም አለ።

የዴሞክራሲ ግንባታው ጅምሩ ጥሩ ነው ያሉት አቶ አባይ “ከሁሉ በላይ ህገ መንግስታችን ምርጥ ከሚባሉት አንዱ ነው፤ በወረቀት ላይ ብቻ አይደለም የተሟላ ነው ባይባልም በተግባርም ረጅም ርቀት ሄዷል” ብለዋል።

ሀገሪቱ ከሁሉ በፊት በእኩልነት እና በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ እንድነትን የሚያረጋግጥ የፌዴራል ስርዓት ዝርግታለችም ብለዋል።

ከሞላ ጎደል የ25 አመታቱ ስኬቶች በዚህ ልክ ሊገለፁ ይችላሉ፤ ግን የክፍለ ዘመን ሩብ በሆነው ጊዜ ከስኬት ጀርባ ጉድለት የለምን?

አቶ አባይ አበይት እና አሳሳቢ የሚባሉ ጉድለቶች ከስኬቱ ጀርባ አሉ ይላሉ።

እናም 25 አመቱ ባለ ሁለት መልክ ነው፤ ባንድ ገፁ የስኬት በሌላኛው ምእራፍ የክፍተት እና ስጋት ምዕራፎች አሉት።

የመልካም አስተዳደር መጓደል እና ይህንን መጓደል አስትንፋሱ አድረጎ እየፋፋ ያለ ኪራይ ሰብሳቢነት ዋነኛው ፈተና ነው።

የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት እና ተግባር የበከለው የመንግስት መዋቅር፣ የድርጅት አመራር፣ አባል እና የህብረተሰብ ክፍል አለ ሲሉም አቶ አባይ ጸሃዬ ይናገራሉ።

የሁለቱን ሰንኮፎች ስረ መሰረት በሁለት መልክ ይሰጡታል።

ከነዚህም ከፊሎቹ ችግሮች ከአመራር ጉድለት የመጡ ሲሆኑ፥ ከፊሎቹ ደግሞ እድገቱ ራሱ የወለደው አዳዲስ ጥያቄዎች ናቸው።

ዋናው ችግር ግን ከፍተኛው አመራር ላይ ነው ያሉ ሲሆን፥ የፓርቲው መካከለኛ እና ዝቅተኛ አመራር እንዲሁም የመግስት ሰራተኛውም መሪውን ነው የሚመስለው።

“ስለዚህ ከላይ ካልተስተካከለ ከታች ምንም ያህል በየጊዜው ብናስተካክለው ለጊዜው ትንሽ ርቀት ይወስደናል እንጂ ስርነቀል ለውጥ አያመጣልንም” ብለዋል።

በቅርቡ የተወሰደው እርምጃው ግን መካከለኛ እና ዝቅተኛው አመራር ላይ አነጣጥሮ የተካሄ ሲሆን፥ ይህ ደግሞ ከፍተኛው አመራር ላይ ለምን እርምጃ አይወሰድም የሚል ጥያቄን ያስነሳል።

አቶ አባይ፥ “ከፍተኛ አመራር ላይ እርምጃ ያልተወሰደበት ምክንያት የእርስ በእርስ የመተራረም እና ከራስ ጀምሮ በህጉና በፖሊሲው መሰረት ራስን ማስተካከል ላይ የቁርጠኝነት ችግር በመኖሩ ነው” ይላሉ።

ለዚህም በምክንያትነት ከሚጠቀሱ ችግሮች ውስጥ “አድርባይነት፣ የእርስ በእርስ አለመተራረም፣ የተነካካ አመራር መኖር እና ለችግሮች ምንም አይነት የሃላፊነት ስሜት የማይሰማው አመራር መኖር ተጠቃሽ ናቸው” ሲሉም ተናግረዋል።

ድርጀቱ ከወገብ በታች የጀመረውን ማጥራት ራስ ወደ ሆነው የድርጅቱ የበላይ አካል የሚወስደው መቼ ነው ለሚለው ጥያቄ፥ አቶ አባይ “ውስጣችንን የሚያከራክረን ይህ ነው፣ አቅቶን ነው ወይስ አይደለም፣ አሁንም ይህን ችግር መፍታት አለብን በቁርጠኝነት ወደ ተግባር መግባት ይኖርብናል” ብለዋል።

ወደ እርምጃ እንግባ እየተባለ ነው ያሉት አቶ አባይ አሁን ለመግባት ሙከራ እየተደረገ ነው ነገር ግን ከዚህ በላይ ገፍተን መግባት ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።

“አሁን የሚስተዋሉት ችግሮች አከቅማችን በላይ አይደሉም” ያሉት አቶ አባይ ጸሃዬ፥ ከሁሉም በላይ የህዝቡ ድጋፍ አለን እንዲሁም ይህን መፍታት የሚያስችል የጠራ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ስላለ ችግሩን በቀላሉ መፍታት ይችላል ብለዋል።