በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የሠቲት ሁመራ እና የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ፀረ-ሰላም ሀይሎች በማንነት ጥያቄ ሽፋን እያራመዱ ያለውን ድብቅ አጀንዳ እንደማይቀበሉት አስታወቁ፡
የድርጊቱ ፈፃሚዎች ላይም መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡
የወረዳው ነዋሪዎች ዛሬ ጸረ ሰላም ሃይሎች በማንነት ጥያቄ ሰበብ እየፈጠሩት ያለውን ሴራ በመቃወም ሰላማዊ ነው ሰልፍ ያካሄዱት።
ፀረ ሰላም እንቅስቃሴን እንቃወማለን ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በዚህ ውስጥ እጃቸውን ባስገቡ ቡድኖች ላይ መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲስድም ጠይቀዋል፡፡
የትግራይ የምዕራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስ ታደሰ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እንደተናገሩት ህዝቡ ለሰላም መረጋገጥ ፣ ለልማትና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሁሌም ትግል ላይ ነው፡፡
”ጸረ ሰላም ሃይሎቹ መልካቸውን እየቀያየሩ የህዝቡን የማንነት መብት ገበያ ላይ ወጥተው ሊሸጡት እየቃጣቸው ነው” ብለዋል፡፡ እንደ ብረት የጠነከረው የክልሉ ህዝብ አቅም፣ የማታገያውን የጠራ መስመርና ያለፈውን የትግል ታሪክ ጽናት በመጠቀም ጸረ ሰላም ሃይሎቹ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ሪፖርተር ፥ ገብረግዚያብሔር ኃይሉ