አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰሞኑን በኤርትራ መንግስት ተጠልፈው የተወሰዱት ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ።
በሻዕቢያ ለቀናት ታግተው የቆዩት ኢትዮጵያውያኑ ትናንት እኩለ ለሊት ላይ ነው የኤርትራን ድንበር ተሻግረው ሱዳን የገቡት።
ከእገታ የተለቀቁት እነዚህ ኢትዮጰያዊያን በአሁን ጊዜ በሱዳን በኩል አደርገው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው።
ሻዕቢያ እነዚህን ኢትዮጵያዊያንን እንዲለቅ ጫና በርትቶበት የቆየ ሲሆን፥ ምናልባትም አሁን የሱዳን መንግስት ሻዕቢያ እነዚህን ኢትዮጰያዊያንን እንዲለቅ ግፊት ሳያደርግበት እንዳልቀረ ነው የሚገመተው።
የኢትዮጵያ መንግስት ኢትዮጵያዊያኑን ከአምባገነኑ የሻዕቢያ መንግሰት ለማስለቀቅ አፀፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁ ይታወሳል።