Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ከህወሓት ፅሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ

ለተጊቢ ጥያቄዎች ዓፈናና ግድያ ምላሽ ኣይሆንም!!

የአቢይ አህመድ አሃዳዊ አምባገነን መንግስት ከኢትዮዽያ ህዝቦች ከተለያየ ኣቅጣጫ እየቀረበበት ያለውን ተቃውሞ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ኣሃዳዊ የግለሰብ አምባገነን ስርዓትን ለመትከል በብልፅግና ፓርቲ ስም የተጀመረው ሃገር የማተራመስ ስትራቴጂ በበርካታ የኢትዮዽያ አከባቢዎች ያስነሳውን ጠንካራ ተቃውሞ፣ ለሚቀርቡ ህጋዊና ተገቢ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ መስጠት ባህርይው የማይፈቅድለት፣ የአቢይ አህመድ አሃዳዊ አምባገነን አስተዳደር በራሱ የተወናበደ አመራር ለተፈጠሩ ችግሮች ሌሎች ወገኖችን ተጠያቂ ማድረግ አሁንም ቀጥሎበታል።

አሁንም ህዝቦች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ምላሹ አፈና፣ የህዝብ ጥያቄ አንግበው የተነሱ መሪዎችን ማሰር፣ ሕጋዊና ሰላማዊ ፖለቲካን አምነው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ማሰደድ፣ ማሰርና መግደልን ነው። የወላይታ ህዝብ የጠየቀውን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ሕገመንግስዊ ጥያቄ ለማፈን ያስችሉናል ብሎ ከጥቂት ቀናት በፊት የወሰዳቸው እርምጃዎችም ከዚህ አፍኝ፣ አሃዳዊ አምባገነን ባህሪው የሚመነጩ ናቸው። ለህዝብ ጥያቄ ያለው ምላሽ ግድያ፣ ማሳደድና እስር እንደሆነ አሁንም በተግባር አረጋግጧል።

ህወሓት ከኢትዮዽያ ብሄር፣ ቢሄረሰቦችና ህዝቦች ጥያቄዎች ጋር ተያይዞ ያለው አቋም ግልፅ ቢሆንም የአቢይ አህመድ መንግስት ራሱ ለፈጠራቸው ችግሮች ህወሓትን ተጠያቂ ማድረግ መቀጠሉ ጥያቄውን ላነሱት ህዝቦች ያለውን ንቀት በግልፅ ያሳየ ተግባር መሆኑን ሁሉም ኢትዮዽያውያን ልብ ሊሉት ይገባል። ላለፉት በርካታ ሳምንታት በኦሮምያም ሆነ በአዲስ ኣበባ እያደረጋቸው የመጡት አምባገነናዊ እርምጃዎች አሁንም ቀጥለው የወላይታን ህዝብ ለማፈን የወሰዳቸው ህገወጥ የአፈና እርምጃዎችን አሁንም በሁሉም ወገኖች ሊወገዝ የሚገባው እንደሆነ ህወሓት ያምናል።

በዚህ አጋጣሚ በንፁሃን ዜጎች ላይ ለደረሰው ግድያ፣ እስርና መንገላታት ያለንን ሃዘንና ተቀውሞ እየገለፅን ይህ ፀረ ሕገመንግስት፣ ፀረ ዴሞክራሲ እና አሃዳዊ አምባገነን ቡዱን በኢትዮዽያ ህዝቦች ላይ እያካሄደ ያለውን መሰሪ ተግባር በአስቸኳይ ለማስቆም እንዲቻል ከወላይታም ሆነ ከሌሎች ጭቁን ህዝቦች ጎን እንደሚቆም ህወሓት ለማረጋገጥ ይወዳል።

የህወሓት ፅሕፈት ቤት
ነሓሰ 05/2012
መቐለ