Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ኦነግና ኤፌኮ ጥምረት ለመፍጠር ውይይት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጥምረት ለመፍጠር ውይይት ማድረግ መጀመራቸው ተነግሯል።

በቅርቡ ከኤርትራ ወደ ሀገር የመጡት የኦነግ ልኡክ አባል የሆኑት አቶ ኢብሳ ነገዎ፥ የኦነግ አመራርን ለመቀበል እየተደረገ ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ወቅት ነው ይህንን ያስታወቁት።

አቶ ኢብሳ በመግለጫቸው፥ መቀመጫቸውን ኤርትራ ያደረጉ የኦነግ አመራሮች በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱ እና የአቀባበል ኮሚቴ መቋቋሙን አስታውቀዋል።

ከኤርትራ ወደ ሀገር የሚመለሰውን ልኡክንም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እንደሚመሩትም ገልፀዋል።

አቶ ኢብሳ በመግለጫቸው አክለውም፥ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ የኦሮሞን ህዝብ ትግል ማጠናከር እንደሆነም ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅትም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ጋር ጥምረት ለመፍጠር የሚያስችለውን ውይይት እያደረገ ነውም ብለዋል አቶ ኢብሳ በመግለጫቸው።