Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አካባቢ ሞተው ተገኙ፡፡


ሐምሌ 17/2010

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አካባቢ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ፡፡
ፖሊስ የአሟሟታቸውን ሁኔታ ለማወቅ ህይወታቸው አልፎ በተገኘበት መኪና ውስጥ የፎሪንሲክ ምርምራ በማድረግ ላይ መሆኑንም ሪፖርተራችን አለማየሁ ታደለ ገልፆልናል፡፡
ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በኢትዮጵያ የሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ስራዎች ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ ሲሆን ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስም የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር፡