Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ስብሰባውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ስብሰባውን ያካሂዳል።

የኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የህዝብና የውጭ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሳዳት ነሻ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ኮሚቴው ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የ2 ዓመት ተኩል አፈፃፀም ይገመግማል።

ግምገማውንም መሰረት አድርጎ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎም ነው የሚጠበቀው።