Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የደኢህዴን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2010 (ኤፍቢሲ) ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የደኢህዴን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ፡፡

ፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳረጋገጠው የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ባካሄደው ምርጫ ነው ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን በሊቀመንበርነት የመረጠው፡፡

ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በአሁኑ ወቅት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ከሁለት ወራት በፊት የቀድሞው የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ የስራ መልቀቂያ ለምክር ቤቱ ማቅረባቸውን ተከትሎ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በአፈ ጉባዔነት መመረጣቸው የሚታወስ ነው፡፡

ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ማናቸው?

የትውልድ ቦታ፦ ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ጅማ ከተማ
የትምህርት ዝግጅት፦

በትራንስፎርሜሽናል ሊደርሺፕ እና ለውጥ አመራር ሁለተኛ ዲግሪ
በግብርና ኤክስቴንሽን የመጀመሪያ ዲግሪ
በጀንደር ኤንድ ዴቭሎፕመንታል ስተዲስ የድህረ ምረቃ ዲፕሎማ የስራ እና የፖለቲካ ተሳትፏቸ
ከ2003 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማእከል በሚኒስትር ማእረግ የጥናት ምርምር እና ፐብሊኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ
በመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ በሚኒስትር ማእረግ ምክትል ፕሬዚዳንት
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ደኤታ
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
የኤፌዴሪ የሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር
በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የሴቶች እና ወጣቶች ዋና ክፍል ሀላፊ
በደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በካቢኔ ማእረግ የርእሰ መስተዳደሩ የህዝብ አደረጃጀት እና ተሳትፎ አማካሪ
በደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሃላፊ
በደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የህዝብ አደረጃጀት እና ተሳትፎ ምክትል ሀላፊ
በደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በጉራጌ ዞን አበሽኬ ወረዳ የህብረት ስራ ማህበራት አደራጅ ኤክስፐርት ሆነው አገልግለዋል።