Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ከደኢህዴን ምክትል ሊቀመንበርነት በገዛ ፈቃዳቸው ሲለቁ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ ተክተዋቸዋል


አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ምክትል ሊቀ መንበርነት በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ።

የደኢህዴን ጽህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው፥ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የመልቀቂያ ጥያቄያቸውን በማቅረብ ነው ከሀላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው የለቀቁት።

አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የደኢህዴን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ባሳለፍነው የካቲት ወር እንደነበረም ይታወሳል።

በምትካቸዉም አቶ ሚሊዮን ማትዮስ የደኢህዴን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

በትናንትናው እለትም አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ሊቀ መንበርነት በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ይታወሳል።

በምትካቸውም ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የደኢህዴን ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።