Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ ወሰነ

አዲስ አባባ፣ ሰኔ፣ 23፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ ወሰነ።

ምክር ቤቱ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር (ኦነግ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና ግንቦት ሰባት የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የሽብርተኝነት ፍረጃ እንዲነሳ ነው የውሳኔ ሀሳቡን ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል።

ምክር ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ሀሳብም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ በሰለማዊ መንገድ እንዲሳተፉ የሚያበረታታ መሆኑንም ገልፀዋል።