Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የወጣቶች የሰላም ኮንፈረንስ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት፣ 04፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወጣቶች የሰላም ኮንፈረንስ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ነገ እንደሚጀምር የትግራይ ክልል የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ነጋ አሰፋ ገለጹ።

በኮንፈረንሱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደረና ከሌሎች ክልሎች የተውጣጡ ከ1500 በላይ ወጣቶች እንደሚሰተፉም ነው አቶ ነጋ አሰፋ የተናገሩት።

በሰላም ኮንፈረንሱ ወጣቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያገጥሙአቸው የኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ችግሮች በዝርዝር እንደሚዳሰሱና ውይይት እንደሚደረግባቸው አቶ ነጋ አስረድተዋል።

በዚህም ወጣቶች የችግሮቹ መንስኤ ሳይሆኑ የመፍትሄ አካል በመሆን በሰላም ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ከመንግስት ጋር አብረው መስራት ስለሚችሉበት ጉዳይ ምክክር ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የተገለጸው።

ኮንፈረንሱ ከግንቦት 5-7፣ 2010 ዓም ለ3 ቀናት እንደሚካሄድም ታውቋል።