Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

አምስት የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጡረታ እንዲያርፉ ተደረገ


አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አምስት የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጡረታ እንዲያርፉ መደረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጽህፈት ቤቱ፥ ሀገሪቱ እያካሄደች ያለችው ሪፎርም የተሳካ እንዲሆን የማድረጉ ስራ እንዲሁም ለህዝቡ የልማትና ለውጥ ፍላጎት ተገቢ ምላሽ የመስጠቱ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያግዙ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ ብሏል።

ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እያካሄዱት ያለው የካቢኔ ለውጥ እንደሚገኝበትም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በአዳዲስ ኃላፊዎች እንዲመሩ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ያለው ጽህፈት ቤቱ፥ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለበርካታ ዓመታት በመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም በጡረታ እንዲያርፉ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት በጡረታ እንዲያርፉ የተደረጉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች

1. አቶ ስብሐት ነጋ- የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል

2. ዶክተር ካሱ ኢላላ- ከፖለሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል

3. አቶ በለጠ ታፈረ- ከተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም፣ ዕቅድና ፖሊሲ ዝግጅት ፕሮጀክት

4. አቶ ታደሰ ኃይሌ – ከንግድና ኢንዱስትሪ የፖሊሲ ዕቅድ አፈጻጸምና ክትትል

5. አቶ መኮንን ማንያዘዋል- ከፖሊሲ ምርምር ማዕከል

በቀጣይም ረዥም ጊዜ በመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉ በጡረታ እንዲያርፉ የማድረጉ ሥራ እንደሚቀጥልም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።