Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ16 የካቢኔ አባላትን ሹመት አጸደቀ

ሚያዝያ 11/2010

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያቀረቧቸውን ሚኒስትሮች ሹመት አፀደቀ፡፡

ፓርላማው ውይይት ካደረገ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ሹመታቸውን ያፀደቀው የ16 የካቢኔ አባላት ናቸው፡፡

በተጨማሪም የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ በወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ተተክተዋል፡፡

አዲስ የተሾሙት የካቢኔ አባላት በፓርላማው ቃለመሃላ ፈፅመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሷሚዎቹ ሁለት አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ትኩት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

የካቢኔ አባላቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ውስንነትንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

ዶክተር አብይ ሚኒስትሮቹ ሙስናን በተጠናና በተደራጀ መንገድ እንዲዋጉም አሳስበዋል፡፡