Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ምክር ቤቱ ነገ አዲስ አፈጉባኤ ይመርጣል፤ የካቢኒ አባላት ሹመትንም ያፀድቃል

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2010 (ኤፍቢሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው መደበኛ ስብሰባ አዲስ የምክር ቤቱን አፈጉባኤ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚያቀርቧቸውን እጩ የካቢኒ አባላት ሹመትን ተቀብሎ ያፀድቃል ተብሎም ነው የሚጠባቀው።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት ስልጣንና ተግባር እንደገና ለማሻሻል የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅንም ተመልክቶ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።