Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ የሚታወቀው የወንጀል መመርመሪያ ማዕከል ተዘጋ


አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ የሚታወቀው የወንጀል መመርመሪያ ማዕከል ተዘጋ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በማዕከሉ እየተመረመሩ የነበሩ የመጨረሻዎቹ እስረኞች ሙሉ በሙሉ ወደ ሌላ ማረሚያ ቤት ተዘዋውረዋል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በታህሳስ ወር ለ17 ቀናት ባደረገው ስብሰባ ካስተላለፋቸው ውሳኔዎች ውስጥ ማዕከላዊን መዝጋት አንዱ እንደነበር ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ካለፈው ዓመት መጨረሻ ጀምሮ በማዕከላዊ የነበሩ ቢሮዎች ካዛንቺስ ወደሚገኘው አዲስ ቢሮ መዘዋወሩ ይታወቃል።

ማዕከላዊ ይሰጥ የነበረውን እስረኞችን የማቆየትና የመመርመር ስራም ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ አቁሟል።

የኢህአደዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ማዕከላዊ ወደፊት ወደ ሙዚየምነት ይቀየራል መባሉ ይታወሳል።