Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን የስልጣን መልቀቅን ጥያቄን መቀበል አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሀገሪቱ ለተከሰተው ችግር መፍትሄ ለመስጠት የቻሉትን ማድረጋቸውን ተናግረው፥ አሁን ስልጣን የሚለቁትም የችግሩ መፍትሄ መሆን ስለፈለጉ እንደሆነ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የስልጣን ሽግግር እስከሚደረግ ድረስ በስራቸው እንደሚቀጥሉ ገልፀው የሀገሪቱ ህዝቦች በተለይም ደግሞ ወጣቶች ሀገሪቱ የምትታወቅበትን ሰላምና ልማት ለማስቀጠል የድርሻቸውን እንዲወጡ አደራ አስተላልፈዋል።