Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የ574 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ


አዲስ አበባ ፣ ጥር 30 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችንና ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

የክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችንና ተጨማሪ በጀት በማጽደቅ በዛሬው እለት አጠናቋል።

ምክር ቤቱ ሶስት የቢሮ ሃላፊዎችን ሹመት ሲያጸድቅ ለአንድ የቢሮ ሃላፊ ደግሞ እውቅና ሰጥቷል።

በዚሁ መሰረት፦

አቶ አማኑኤል አሰፋ- የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ
አቶ ነጋ አሰፋ- የክልሉ የወጣቶች ጉዳይና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ
አቶ ረዳኢ ሃለፎም የህዝብና መንግስት ግንኙነት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሾመዋል።
ምክር ቤቱ ከዚህ ባለፈም የዶክተር አትንኩት መዝገቡን ለክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ሃላፊነት እውቅና ሰጥቷል።

እንደዚሁም ምክር ቤቱ 574 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀትም በዛሬው ማጠናቀቂያው ላይ አፅድቋል።