Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በቆቦ ከተማ በተፈጠረ ግጭት የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ


አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ በተፈጠረ ግጭት የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አማረ ጎሹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ትናንት እና ዛሬ በተፈጠረው የፀጥታ ችግርም ሁለት ሲቪል ሰዎች እና አንድ የፀጥታ ሀይል ናቸው።

ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ በዘጠኝ ሰዎች ላይም ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ነው ሀላፊው የገለጹት።

የግጭቱ መንስኤ እየተጣራ መሆኑን የተናገሩት ኮማንደር አማረ፥ በመንግስት ተቋማት፣ በግለሰቦች እርሻ፣ ተሽከርካሪዎች እና በሌሎች ግለሰቦች ንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ጠቁመዋል።

የቆቦ ከተማን ፀጥታ ለማስጠበቅ በዛሬው እለት ከወጣቶች፣ ከሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት መደረጉንና በአሁኑ ወቅት በከተማዋ መረጋጋት እንደሚታይም ነው ያብራሩት።