Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ


አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ ሾመ።

ዶክተር ደብረፅዮን የምክር ቤቱ አባል ባለመሆናቸው በክልሉ ህገመንግስት መሰረት ርእሰ መስተዳድር ሆነው መሾም ስለማይችሉ ነው በምክትል ርእሰ መስተዳደርነት የተሾሙት።

ሆኖም የክልሉን መንግስት ካቢኔ የመምራት እና የርእሰ መስተዳድሩን ሀላፊነት ተክተው መስራት እንደሚችሉ ተመልክቷል።

ዶክተር ደብረፅዮን በምክትል ርእሰ መስተዳደርነት በምክር ቤቱ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

የቀድሞው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ በስንብት ንግግራቸው አብረዋቸው የሰሩ የተለያዩ አካላትን አመስግነው፥ አሁን ከተሾመው አስተዳደር ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።