Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ጥሎት የነበረውን ማእቀብ አራዘመ


አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ እና ሶማሊያ ላይ ጥሎት የነበረውን ማእቀብ ለተጨማሪ አንድ ዓመት አራዘመ።

በኤርትራ እና ሶማሊያ ያለውን ሁኔታ እንዲያጣራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያቋቋመው አጣሪ ቡድን የአስመራ መንግስት አሁንም ኢትዮጵያን እና ጅቡቲን የሚቃወሙ ታጣቂ ቡድኖችን እንደሚያስታጥቅ በሪፖርቱ አስታውቆ ነበር።

ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ ተዘጋጅቶ ዛሬ ለፀጥታው ምክር ቤት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በኤርትራ እና ሶማሊያ ላይ ተጥሎ የቆየው ማእቀብ እንዲራዘም የሚጠይቅ ነው።

በውሳኔ ሀሳቡ ላይ የመከረው ምክር ቤቱ በ11 የድጋፍ ድምፅ እና በ4 ታቅቦ ማእቀቡን ለአንድ ዓመት አራዝሟል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛው አምባሳደር ዶክተር ተቀዳ ዓለሙ እንደተናገሩት፥ የምክር ቤቱ ውሳኔ ለአካባቢው ሰላም እና ፀጥታ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የኤርትራ መንግስት የተጣለበትን ማእቀብ በመተላለፍ አሁንም የአከባቢውን ሰላም የሚያደፈርሱ ታጣቂ ቡድኖችን እያስታጠቀ መሆኑን በማንሳት ይህ እንዲሁ የሚታለፍ አለመሆኑን ነው የተናገሩት።