Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ600 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ


አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለምትተገብረው የሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር የሚውል የ600 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገ።

በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው የገጠር ነዋሪዎች ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ እየተተገበረ የሚገኘው የሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር መተገብር ከጀመረ 12 ዓመት ተቆጥረዋል።

በአሁኑ ወቅትም 8 ሚሊየን ዜጎች የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ሲሆኑ፥ ከዚህ ውስጥ 4 ሚሊየኑ ኤል ኒኖ በፈጠረው ድርቅ ምክንያት ለምግብ እህል እጥረት በተጋለጡ አከባቢዎች የሚገኙ ናቸው።

መርሃ ግብሩ በምግብ ለስራ በርካቶች የአከባቢ ጥበቃን ጨምሮ በተለያዩ የልማት ስራዎች በመሳተፍ ድጋፉን በማግኘት ራሳቸውን በምግብ እህል እንዲችሉ አድርጓል።

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ካሮሊን ተርክ መርሃ ግብሩ የሰብዓዊ እርዳታ ከልማት ስራ ጋር እንዴት መተሳሰር እንደሚችል ያሳየ፤ ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።

ይህ የዓለም ባንክ የአሁኑ የገንዘብ ድጋፍ ለድርቅ አደጋ የሚሰጠውን ምላሽ በመደገፉ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ባንኩ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።