Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከእሁድ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ


አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 19 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሮ ኮኖ ከእሁድ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ ሚኒስትሮቹ የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታና በተለያዩ የዓለም አቀፍ የደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ።

ታሮ ኮኖ ጃፓን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የ100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ኢትዮጵያና ጃፓን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጀመሩ አንድ ምዕተ ዓመት ሊሞላቸው ነው።