Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ቦርዱ የአማራና ቅማንት ማህበረሰብ ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራና ቅማንት ማህበረሰብ ተወላጆች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ ላማካሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ፡፡

ህዝበ ውሳኔው የሚካሄደው የፌድሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩን ተመልክቶ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል።

የአማራ ክልል ካቢኔ ሰሞኑን የቅማንት ማህበረሰብ የራሱ አስተዳደር እንዲኖረው ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም የአስተዳደር ወሰን ለማካለል የአማራና ቅማንት ብሄረሰብ ተወላጆች እንደ ምርጫቸው፥ በፈለጉት አስተዳደር ስር እንዲሆኑ ህዝበ ውሳኔ መዘጋጀቱም ተነግሯል።

ህዝበ ውሳኔውን የማስፈፀም ሃላፊነት የተሰጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ወደ ቀበሌዎቹ የቴክኒክ ቡድን መላኩን፥ የቦርዱ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተስፋ ዓለም አባይ ተናግረዋል።

የህዝበ ውሳኔው ማካሄጃ ጊዚያዊ መርሃ ግብር የተዘጋጀ ሲሆን፥ በቦርዱ እና በክልሉ መንግስት ተመክሮበታል።

መርሃ ግብሩን በቅርቡ አፅድቆ ይፋ እንደሚያደረግ ያሳወቀው ምርጫ ቦርድ፥ በህዝበ ውሳኔው እስከ 25 ሺህ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አመላክቷል፡፡