Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ

haileselassie-gebre
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴን የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንትነት አድርጎ መረጠ።
በምርጫው ሀይሌ ዘጠኝ ድምፅ ሲያገኝ አቶ ተፈራ ሞላ አምስት ድምፅ እና አቶ ዳኛቸው ሽፈራው አንድ ድምፅ አግኝተዋል።
ፌዴሬሽኑን ለአራት አመታት በፕሬዚዳንትነት ለመምራት የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በመወከል አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ፣ ትግራይ ክልልን በመወከል አቶ ወልደገብርኤል መዝገቡ፣ የደቡብ ክልልን በመወከል አቶ ተፈራ ሞላ የኦሮሚያ ክልልን በመወከል ዳኛቸው ሽፈራው እና የጋምቤላ ክልልን ወይዘሮ አለሚቱ ኡመድ ወክለው በእጩነት ቀርበው ነበር።
ሆኖም ከምርጫው በፊት ትግራይ ክልልን በመወከል ቀርበው የነበሩት አቶ ወልደገብርኤል መዝገቡ እና የጋምቤላ ክልልን የወከሉት ወይዘሮ አለሚቱ ኡመድ ራሳቸውን አግልለዋል።
ጠቅላላ ጉባኤው የስራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ በማካሄድ ላይ ነው።
ለስራ አስፈጻሚነት ደግሞ ከአትሌቶች ደራርቱ ቱሉ ከአዲስ አበባ፣ አትሌት ገዛኸኝ አበራ ከኦሮሚያ፣ አትሌት ገብረእግዚአብሄር ገብረ ማርያም ደግሞ ከትግራይ ክልል እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸው የሚታወስ ነው።