Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ፖሊስ የደመራ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን ገለጸ

demera-2
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተከበረው የደመራ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርአቶች ይከበራል።
በዓሉ ትናንት በመስቀል አደባባይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የውጭ ሀገር መንግስታት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና የውጭ ሀገር ዜጎች በተገኙበት ተከብሯል።
በደመራ ማብራት ስነ ሥርዓቱ ላይ የእምነቱ ተከታዮች፣ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች በተለይም የከተማዋ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር በመተባበር ስነ ስርአቱ ፍፁም ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውንም ኮሚሽኑ በመግለጫው አመልክቷል።
የእምነቱ ተከታዮች ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ለሠላም እውን መሆን ላደረጉት ቀና ትብብርም ምስጋናውን አቅርቧል።
ኮሚሽኑ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓል የሠላምና የደስታ እንዲሆን መመኘቱን ኢዜአ ዘግቧል።