Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የ11ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤት እድኞች ከዛሬ ጀምሮ የውል ስምምነት ይፈራረማሉ

addis-cond
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 9 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ የ11ኛው ዙር እጣ የወጣላቸው 37 ሺህ የሚሆኑ የጋራ መኖሪያ ቤት እድኞች ከዛሬ ጀምሮ የውል ስምምነት እንደሚፈራረሙ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
ከባንክ፣ ካርታና ተያያዥ መረጃዎች ጋር ተያይዞ እድለኞች ይወስድባቸው የነበረውን ረዥም ጊዜ ለማስቀረት፥ ቢሮው ሁሉንም አገልግሎት በአንድ አካባቢ የያዙ ማዕከላትን አቋቁሟል።
ከዚህ ቀደም የቤት እድለኞች ከከተማ አስተዳደሩ በእጣ የወጣላቸውን ቤት ቁልፍ ለመረከብ እስከ አንድ አመት ጊዜ ይወስድባቸው ነበር።
ይህም እድለኛው የቤት ባለቤትነቱን ለማረጋገጥ እና ቁልፉን ለመረከብ የማረጋገጫ እና የክፍያ ሂደቱን የሚፈጽምበት አሰራር በተለያዩ ተቋማት የሚሰጥ በመሆኑ ምክንያት ነው።
ይህን ችግር ለመቅረፍም ቢሮው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የአንድ ማዕከል አገልግሎትን አቋቁሟል።
ለዚህም በቦሌ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ማዕከላትን በማቋቋም ከዛሬ ጀምሮ ደንበኞችን ለማስተናገድ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
እድለኞቹ ከዚህ በፊት በወራት ይጠናቀቅ የነበረውን አገልግሎት በአንድ ቀን እንደሚያገኙም ነው የየክፍለ ከተሞቹ የስራ ሃላፊዎች የገለጹት።