Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አዲስ የድርጅቱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር መረጠ

opdo-mark

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመስከረም 04 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለስድስት ቀናት ጥልቅ የተሃድሶ ግምገማ ሲያካሂድ ሰንብቷል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ያካሄደውን ጥልቅ የተሃድሶ ግመገማ ተከትሎ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሙክታር ከድር እና ምክትላቸው ወይዘሮ አስቴር ማሞ ራሳቸውን ከሃላፊነት አንስተዋል።
ይህንንም ተከትሎ አቶ ለማ መገርሳን የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ማዕከላዊ ኮሚቴው መርጧል።
የማዕከላዊ ኮሚቴው ውሳኔዎች ዝርዝር መረጃን የምናቀርብ ይሆናል

lammaa magarsaa

lammaa magarsaa


workneh gebeyehu

workneh gebeyehu