Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በባህር ዳር ስብሰባውን እያካሄደ ነው

ANDM
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ በባህር ዳር ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

ትናንት ቀትር ላይ የጀመረው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን፥ በተለይም ባለፉት 15 አመታት የተሰሩ ስራዎችን እና የተገኙ ውጤቶችን እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮች እና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ውይይት እያደረገ ነው።

የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አለምነው መኮነን እንደገለፁት፥ በስብሰባው ነባር እና ወቅታዊ ጉዳዮች ሰፊው የውይይት ጊዜ የሚሰጣቸው ሲሆን፥ የ2008 እቅድ አፈፃፀምና የ2009 እቅድም የሚገመገም ይሆናል።

ሀላፊው አክለውም ኮሚቴው በሁሉም አጀንዳዎች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ የተለያዩ ውሳኔዎችንም ያሳልፋል ብለዋል።

እስከ ጳጉሜ 5 የሚቆየው ስብሰባው ብአዴን ጥልቅ የተሀድሶ ንቅናቄውን የሚጀምርበት እንደሆነም ነው አቶ አለምነው የተናገሩት።