Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ኢትዮጵያዊው አበበ አዕምሮስላሴ በአይ ኤም ኤፍ የአፍሪካ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

href=”https://alphanegari.com/wp-content/uploads/2016/09/at-abebe-IMF.jpg”>at-abebe-imf
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አበበ አዕምሮስላሴ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ገለፀ።
የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስ ክርስቲን ላጋርድን ጠቅሶ ይፋ እንዳደረገው አቶ አበበ አዕምሮስላሴ የአፍሪካ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።
አቶ አበበ አፍሪካን በሚያጋጥሟት ችግሮች ላይ ያላቸው ጥልቅ እውቀትና ከፖሊሲ አውጭዎች ጋር በቅርበት መስራታቸው ተመራጭ አድርጓቸዋልም ተብሏል።
የመሪነት ሚናቸው፣ አስተባብሮ በማሰራትና ትንታኔ የመስጠት ችሎታቸውም ተጠቅሷል።
አቶ አበበ ከአሁን በፊት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ዲፓርትመንት ምክትል ዳይሬክተር እንዲሁም በተለያዩ አገራት የድርጅቱ ተወካይ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
አዲሱን ስራቸውንም መስከረም 10 ቀን 2009 ዓ.ም ይጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ በዘገባው አመላክቷል።