Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከላይ አርማጮሆ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

gedu
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የላይ አርማጮሆ ወረዳ ነዋሪዎችን የወልቃይት ጠገዴን የማንነት እና የወሰን ጉዳይን በተመለከተ አወያዩ።

ርዕሰ መስተዳደሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት የጠገዴን እና ፀገዴን ወሰን ሁለቱ ክልሎች ተናጋግረው በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ ይሰጣሉ ብለዋል።

በጐንደር የሚኖሩ የወልቃይት ነዋሪዎች ጥያቄቸውን በሰለማዊ ሁኔታ የማቅረብ መብት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የታሰሩትም በግልፅ ጉዳያቸው እንዲታይ እና ቤተሰቦቻቸው እንዲጠይቋቸው ይደረጋል ማለታቸውን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።