Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለግድቡ የ6 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የቦንድ ሽያጭ ለማድረግ ታቅዷል

abay-bond-sale
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 8 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ሀገራት ላሉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ6 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የቦንድ ሽያጭ ለማድረግ ማቀዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በዚህና በሌሎች ሀገራዊ ልማት ጉዳዮች ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመቶ የሚቆጠሩ ምክክሮችን አድርጓል።
ባለፈው አመት ለዳያስፖራው አባላት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ6 ነጥብ 2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ቦንድ ለመሸጥ አቅዶ የ5 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ቦንድ መሸጡን ተናግረዋል።

በዚህ አመት የታቀደውን የቦንድ ሽያጭ ለማሳካት ዝግጅት መደረጉንም ነው የተናገሩት።