Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በሀገሪቱ ፈጣን የኢኮኖሚ መዋቅር ለውጥ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

stractural-change
የኢኮኖሚ ዕድገቱ እስከአሁን ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ ማለፉም ተገልጿል፡፡

በጉዳዩ ላይ አለም አቀፉ የዕድገት ማዕከል ከኢትዮጵያ የልማት ጥናት ተቋም ጋር በመተባበር ውይይት ተካሂዷል፡፡

የስራ እድል ፈጠራና ተያያዥ ጉዳዮች፣ የማሕበራዊ ለውጥ አንቀሳቃሾች ሚና፣ በገጠርና በከተማ መካከል ያለው የገበያ ትስስር ለኢኮኖሚ ያለውሚናና ሌሎችም ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ውይይቱ ያተኮረባቸው ጉዳዮች ናቸው።

በአለም አቀፍ የዕድገት ማዕከል የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ስዩም እንዳሉት እነዚህ ጉዳዮች በአገሪቱ ዋና ዋና የኢኮኖሚ እቅዶች ውስጥ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ ያሻል።

ይህን በማድረግም እየተመዘገበ ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ፈተናዎችን ተቋቁሞ በተከታታይነት እንዲዘልቅ ያስችላል ብለዋል።

ይህን ለማሳካት መዋቅራዊ ለውጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው ምርታማነትን ማሳደግ፣ በተገኘው ምርት ፍትሀዊ ክፍፍል መፍጠርና የካፒታልና ተቋማዊ አቅምን መገንባት መሰረታዊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር አብርሀም ተከስተ የአገሪቱን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማያቋረጥ ሁኔታ ለማስቀጠልና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ አወቃቀሩ ለውጥ ማፈጠን አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የኢኮኖሚ ዕድገት ድርቅንና አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ለውጦችን መቋቋም ማስቻሉንም ገልጸዋል።

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን መዋቅራዊ ለውጡን ለማሳካት እንዲቻል በዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ የግሉን ዘርፍ የማጠናከርና አምራች ኢንዱስትሪዎችን የማስፋፋቱ ተግባር ትኩረት እንደተሰጠው ተገልጿል።

One Response to በሀገሪቱ ፈጣን የኢኮኖሚ መዋቅር ለውጥ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ