Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

“ሰላም ይቅርና ሰው ልጅ ወፍም ትወዳታለች’’

flying-bird
“ሰላም ይቅርና ሰው ልጅ ወፍም ትወዳታለች’’
በያሬድ ኣለምሰገድ 06/01/2009 ዓ/ም
መንግስት መሆን የማይፈልግ እጁን ያውጣ? መንግስት ማለት ህዝብነው ፤መንግስት የህዝብ ቅጥረኛ ነው፤መንግስት በህዝብ ድምፅ ውክልና የተሰጠው የሰዎች ስብስብ ነው…ብሎ ማሰብ መልካምነት ፤ጥበብና ስልጣኔ ነው፡፡የህዝብ ውክልና ለማግኘት ግን ፀድት ፍክት ያለ ፖሊሲና ስትራተጂ እንዲሁም ፖለቲካዊ ምህዋሩ በተረጋጋና የአገሪትዋ እድገት በሚያረጋግጥ መልኩ የሚያሰራ የመንግስት መዋቅር አፈፃፀም ህግና ደንብ የለየ ብቁ የአጭር፤መካከለኛና ረጅም እቅዶች ማዘጋጀትና ህዝብ እንዲያውቀው ማድረግ የግድ ይላል፡፡
መንግስት ለመሆን ህገ-መንግስት እንደ ምንጣፍ በመርገጥ፤እንደ ቅርፊት ልጦ በመጣል ሳይሆን…አንድ ብሄር ከአንድ ብሄር በማስበለጥ ሳይሆን…ጥቅሞች በማጥላላት ሳይሆን የተገኙት አመርቂ የሰላምና የብልፅግና ጉዞ በተቻለ መልኩ እየደገፍክና እየገመገምክ መሄድ ይጠይቃል፡፡
አባይን የመሰለ ትልቅ ታሪካዊ ሃውልት በመቃዎም፤የህዝቦች አብሮነትና መፈቃቀር በመበጥበጥ፤ታሪክ ከማይረሳቸው የአገራችን ጠላቶች ጎን በመሰለፍ የጥፋት ተልእኮቻቸው በማሳካት በተላላኪነት በማገልገል፤የተገኘው ሰላም በማደፍረስና ልማቱን በማዳቀቅ…የኢትዮጵያውያን ባህልና ታሪክ በማዳቀል መንግስትነት ይሳካል ብሎ ማሰብ በኔ በኩል ስህተት ነው፡፡ዞሮዞሮ መንግስትነት ማረጋገጥ የሚቻለው ከላይ እንደተጠቀሰው በሰላማዊ መንገድ ህገ-መንግስቱን በማክበርና በማስከበር ጭምር አንድ ብሄር ከሌላኛው ብሄር በቋንቋ በባህልና እምነት እኩል መሆኑን በማመን ብቻ መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡
ለመንግስትነት ያን ያህል መጨነቅ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ምክንያቱም መንግስት ለመሆን አልያም የስልጣን ጥማት ለማርካት የሚያስችሉ ነገሮች እጅግ ቀላል በመሆናቸው፡፡አንዳንድ ሰዎች ስልጣን ለማግኘት ከሚገምቱት በላይ አድርገው ይመለከቱታል፡፡እንደማይሆን ሲመስላቸው ወደ ጥፋት ሽብርተኝነትና ብጥብጥ ይገባሉ…ከገመቱት በታች ሲሆንም እንዲሁ፡፡ከላይ እንደተገለፀው አንድ መንግስት የህዝብ ቅጥረኛ ነው ከተባለ ስልጣን የመንግስት ነው ማለት ነው፡፡ስለዚህም መንግስት ለመሆን የህዝብ ድምፅ ማግኘት እቅድህ፤ፖሊሲህና ስትራተጂህ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅና አሳማኝ መሆን ይጠበቅበታል፡፡የማንም አገር መንግስት ቀዳዳ አለው፡፡መልካም ስራም እንዲሁ፡፡ተቀናቃኝ ተወዳዳሪ ለመሆን ህዝቦች በእኩልነት ከገዢው ያጡት ነገር በጥናት የተመሰረተ ነቅሶ በማስውጣት የችግሮች መፍትሄ ዘላቂ እቅድ በማውጣት ፤ያቀረብከው መፍትሄ ህዝቦች አምኖውበት እንዲቀበሉ በማድረግ አሸናፊነትህ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡አንድ ነገር ግን አለ የጠባብነትና ትምክህተኝነት አስተሳሰብና ተግባር ከዓላማህ እንዳይምታታ ማስወገድ ይጠበቅብሃል፡፡
ካልሆነ ግን ሰማይ እንዲታረስ ማዘዝ ይሆናል ማለት ነው፡፡አንድ ሴት ልጅ አሳምነክ ለሷ ያለህ አክብሮትና የፍቅር ስሜት ካልገለፅግላት በተግባር ካላስረዳሃት የፍቅር ጓደኛዋ ለመሆን እንደማይቻል ሁሉ መንግስት ለመሆንም እንዲሁ በትእግስት ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በማክበርና በመፈቃቀድ ይሆናል ማለት ነው፡፡ኢህአዴግ ከዚ የተለየ ነገር አልሰራም፡፡ኢህአዴግ ያደረገው ነገር ቢኖር በመፈቃቀርና በመፈቃቀድ ስሜት የተገነባች አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለመገንባት ያለ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩልነትና አብሮነት እንደማይሳካ ቀድሞ በማወቁ ዘመን የማይሽራቸው አለምን ያስደመሙ ፖሊሲና ስትራተጂዎች…የስኬት አቅጣጫዎች ለይቶ በማስቀመጡ ብቻ ነው ለዚሁ ድል ያበቃው፡፡
በመጨረሻ…አንድ ነገር ለማለት እፈልጋለሁኝ፡፡መንግስት ለመሆን ከመፈለጋችን በፊት መንግስት የት ቦታና አንዴት ይገኛል ብሎ ማሰብ ይጠበቅብናል፡፡ከ18 ዓመት በታች የሆኑት ህፃናት በማያውቁት ፖለቲካዊ ውዥምብር ለሽብርና ለብጥብጥ እንዲነሳሱና የህዝቦች ሰላም በመበጥበጥ ህዝቦች በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጡ በማድረግ፤መንግስት በተነሳው እሳት ተንገራግጦ በፍርሃት በድንጋጤ ከዛፍ እንዲወድቅ በማድረግ ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ምክንያቱም ያሁኑ መንግስት ይቅርና እንደ ሾላ ፍሬ በድንጋይ…ይቅርና ዛሬ እስካፍንጫው ዘመናዊ መሳርያ ታጥቆ ትናንትናም እሾህ ሳይሆን ቦምብ እየረገጠ ሚሳኤል በእጁ ማስገባት የሚችል በአንድ ኢትዮጵያዊነት በአንድ ህገ-መንግስት ጥላ የኖረ ምርጥ ሰራዊት ባለቤት በሆነበት ግዜ መሞከር በራሱ ቅዥት ነው፡፡
እናም ቀለል ባለ መልኩ ህገ-መንግስቱን በሚፈቅደው አካሄድ እየተስተናገዱ መንግስት የመሆን ህልምዎ ያሳኩ፡፡ኢትዮጵያ እንደነ ሶርያ ማድረግ ቀላል ነው…ኢትዮጵያ ቆራርጦ በመጣል አባይን ወደ ነበረበት ማፈፍ ይቻላል…ኢትዮጵያ አንድነትዋን ክብርዋን ጥላ ያበደች መናፍቅ በእርዳታ ብቻ የሚኖር ህዝብ እንዲኖራት ማድረግ ቀላል ነው ፍላጎትም ሊኖር ይችላል…ወደ ተግባር ለመግባት ግን የማይፈቅድ በህዝቦች አንድነት በተሰዉ የህዝብ ልጆች አጥንት የተገነባ እንከን የለሽ አስተማማኝ ፌደራላዊ ስርዓትና ኒኩለር የማይበሳው ህገ-መንግስት እስካለ ድረስ አይቻልም፡፡ሰላም ይቅርና ሰው ልጅ ወፍም ትወዳታለች …ይቅርና የሰው ልጅ መጠልያ ቤት የወፍ ቤት ድንጋይ ወርውሮ ማፍረስና ማቃጠል ህገ-መንግስታችን አይፈቅድም፡፡
በዚ አካሄድ መንግስት መሆን አይቻልም፡፡