Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ሰላም ወዳዱ የመዲናዋ ነዋሪ የፀረ- ሰላም ሀይሎችን በሬ ወለደ ቅስቀሳ ወደ ኋላ በማለት መደበኛ ተግባሩን ሲያከናውን መዋሉን ፖሊስ ገለፀ

addis abeba
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፀረ-ሰላም ሀይሎች የአዲስ አበባ ነዋሪ ሰልፍ እንዲወጣ ቢቀሰቅሱም ምንም አይነት ሰልፍ አለመደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ነዋሪው የፀረ- ሰላም ሀይሎችን በሬ ወለደ ቅስቀሳ ወደ ኋላ በማለት የእለት ከእለት ተግባሩን ሲያከናውን መዋሉን ኮሚሽኑ ገልፆ፥ በዛሬው እለት በመዲናችን የነበረው የፀጥታ ሁኔታ ፍፁም ሰላማዊ እንደነበር ኮሚሽኑ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ሰላም ወዳዱ ህዝባችን ከፖሊስ የተላለፈለትን መልእክት በመቀበል እና ተግባራዊ በማድረግ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ጥቆማ በመስጠት እና አካባቢውን በመጠበቅ እያደረገ ላለው ትብብር ምስጋናውን አቅርቦ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በተጨማሪም ህዝቡ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥመው ለፀጥታ ኃይሉ ጥቆማ የመስጠት ልምዱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽኑ ጠይቋል፡፡