Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ በማድረግና ከህዝቦች ጋር በመተባበር በሀገሪቱ የሚታዩ ችግሮችን በአፋጣኝ ይፈታል- ጠ/ሚ ሃይለማርያም

PM

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ መግለጫቸውን የጀመሩት በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በተከሰቱት ሁከቶች እና ግጭቶች የሰው ህይወት እና ንብረት በመጥፋቱ መንግስት የተሰማውን ሀዘን በመግለፅ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም በእነዚህ ክልሎች ለተስተዋሉት ግጭቶች እና ሁከቶች አብይ መንስኤ ናቸው ያሏቸውንም ጉዳዮች አንስተዋል።

ባለፉት ዓመታት አገሪቱ ባስመዘገበቻቸው ፈጣን እድገቶች ህዝቡ በየደረጃው እየተጠቀመ ቢመጣም፥ የእድገቱ ፍጥነት ግን ያመጣቸው ተግዳሮቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በተለይም ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የህዝብ ቁጥር እና ፍላጎት እያደገ በመምጣቱ የሚነሱ ጥያቄዎችን መጨመራቸውን ነው ያነሱት።

የስራ አድል በስፋት አለመፈጠር ለችግሩ መንስዔ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በሀገሪቱ ከ40 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከድህነት ወለል በታች ይገኙ ነበር፤ ከዚህ ውስጥ 20 የሚለየን ያህሉን ከዚህ ችግር ማውጣት ተችሏል፤ አሁንም ግን 20 ሚሊየኑ ከድህነት ወለል በታች ይገኛል ነው ያሉት።

ይህ ህዝብ አሁንም ከዚህ ችግር ለመውጣት ጥያቄ ያቀርባል፤ የስራ እድል እንዲፈጠርለት ይፈልጋል፤ እነዚህ ጥያቄዎች ቶሎ ምላሽ ሳያገኙ ሲቀሩ ጥያቄዎች እንዲነሱ እና ችግሮች እንዲፈጠሩ ያደርጋል ብለዋል።

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠሩ ሁከቶች እና ግጭቶችም መንግስት ህዝብ ላነሳቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ባልመስጠቱ እና ለወጣቶች በቂ የስራ እድል ባለመፈጠሩ የመጡ ናቸው ብለዋል።

በስርዓቱ ውስጥም የመንግስት ስልጣንን በአግባቡ አለመጠቀምን የመሰሉ ችግሮችም እድገቱ በፍጥነት እንዳይሄድ ጎታች ሁኔታዎች ነበሩ፤ ከህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንቅፋት ሆነዋል ሲሉም አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የውጭ ሀይሎች እጅ አለበት የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለዘመናት የአገሪቱን ድክመት የሚመኙ እና ኢትዮጵያ ደካማ ሆና በተፈጥሮ ሀብቷ እንዳትጠቀም የሚፈልጉ አገራት መረጋጋት ለማሳጣት የሚያደርጉት አባባሽ ተፅእኖ አለ ብለዋል።

አገራቱ ገንዘብ በገፍ በውጭ ለሚገኙ ጥቂት ጽንፈኛ የዳያስፖራ አባላት በማከፋፋል ሁከቱ እንዲስፋፋ እያደረጉ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

መንግስት እንዚህን እና መሰል ችግሮችን ለመፍታት በውስጥ እና በውጭ ያሉ ችግሮቹን ለመቅረፍ እንደሚሰራም በመግለጫቸው ላይ አስታውቀዋል።

ከዚህ ውስጥ ዋነኛው መሪው ድርጅት ኢህአዴግ ራሱን በጥልቅ ተሃድሶ ይመለከታል ያሉ ሲሆን፥ ይህን ለማድረግም ባለፈው ሳምንት ባካሄደው የምክር ቤቱ ጉባኤ ባካሄደው ውሳኔ አሳውቋል ብለዋል።

መንግስት ስልጣን ያገኘው ከህዝቡ ነው፤ የተመረጠውም ህዝቡን ሊያገለግል እና የህዝቡን ችግር ለመፍታት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ህዝቡ የሰጠውን ስልጣን በአግባቡ መጠቀም እና ማገልገል ትቶ ለራሱ የሚገልገል ባለስልጣን ግን መኖሩን ነው የተናገሩት።

ለመንግስት ስልጣን ያለው አመለካከት፣ አረዳድ እና አፈፃፀም ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይ ፓርቲው ራሱን በጥልቀት ፈትሾ ያጠራል ብለዋል።

በመሆኑም ህዝብን ለማገልገል የተቀመጠውን መስመር ተከትሎ የማይሄድ አመራር ከመስመሩ መነጠል ስላለበት ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወሰድ አብራርተዋል።

ይህንንም መሰረት አደርጎ በመንግስት አደረጃጀት እና መዋቅር ምደባ በማድረግ ጥቅምት መጀመሪያ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስራውን ሲጀምር ድርጅቱ አዲስ የመንግስት አደረጃጀትን የሚያቀርብ ይሆናል ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይልማርያም የዴሞክራሲ ተቋማትን የማጠናከር ስራም ይከናወናሉ ብለዋል።

ከማንነት እና ከድንበር ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ጥያቄዎች እስካሁን ምላሽ እየተሰጠ መምጣቱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በቀጣይም መሰል ጥያቄዎች በተመሳሳይ መልኩ ይፈታሉ ብለዋል።

የወልቃይት የማንነት ጥያቄን በተመለከተ ጥያቄው መቅረብ የነበረበት ለትግራይ ክልል ነው፤ ለክልሉ እስካሁን ይህ ጥያቄ አልቀረበለትም፤ ከዚህ በኋላ ጥያቄው ቢቀርብለት ግን ክልሉ እንደሚመለከተው አረጋግጠዋል።

ከዚህ ባሻገር በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል መካከል ያለውን የድንበር ጥያቄ በተመለከተም እስካሁን ችግሩ ላለመፈታቱ ተጠያቂዎቹ የየክልሎቹ አመራሮች እንደሆኑ ተናግረዋል።

ህዝቡ እንደ ህዝብ ችግሩን በተደጋጋሚ እያወጣ በጥያቄ መልክ ሲያቀርብ ቆይቷል፤ ጥያቄው ግን ምላሽ አላገኘም ያሉት አቶ ሀይለማርያም፥ ለዚህ የህዝቡ ትእግስት መንግስት ምስጋናውን ያቀርባል ብለዋል።
ሆኖም ግን በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ያላደረጉ አመራሮች ተጠያቂ ይሆናሉ ነው ያሉት።

እዚህም እዚያም በሚታዩ ግጭቶች አገሪቱ ትፈራርሳለች የሚለው ስጋት መሰረተ ቢስ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይልማርያም፥ እንኳን አሁን ይቅርና በቀደሙት ጊዜያቶች ይህች አገር ሳትፈራርስ ቀጥላለች ብለዋል፤ አሁን በአገሪቱ ያለው ስርዓት በአለት መሰረት ላይ መቆሙን በማንሳት።

ኢህአዴግ ችግር ሲገጥመው በራሱ አውቆ እና ህዝቡ ሲነግረው ከእነዚህ ችግሮች በሳይንሳዊ መንግድ ተንትኖ እና ገምግሞ መፍትሄ የመስጠት ብቃቱ ዛሬም እንዳለው ተናግረዋል።

ድርጅቱ ሁልጊዜ ተማሪ መሆኑንም በማንሳት፥ ችግሮቹን እያየ እና እነዚህ ችግሮች ስር ሳይስዱ መፍትሄ እየሰጠ የመጣ ልምድ ያለው እንደመሆኑም አሁን ያለውን ሁኔታ እንደመልካም ሁኔታ ወስዶ ራሱን አድሶ እንደሚሄድ አስታውቀዋል።

አሁን በላው ሁኔታ መንግስት በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥረው የነበሩ ግጭቶችን ከህዝቡ ጋር በመሆን በሰራው ስራ ከሞላ ጎደል በክልሉ አብዛኛው ስፍራ መረጋጋት መፍጠር ተችሏል ያሉ ሲሆን፥ በአማራ ከልል የሚስተዋለውን ችግርም በተመሳሳይ መልኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፈታል ብለዋል።

በመጨረሻም መንግስት ህግ እና ስርዓትን የማስከበር ሀላፊነት እና ህዝብ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት ሙሉ አቅም እንዳለው ተናግረዋ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.