Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በቁጥጥር ስር የሚገኙት የኦብነግ አመራሮች ተልእኮውን ከሻዕቢያ መንግስት መቀበላቸውን ተናገሩ

onbeg
ሐምሌ 15፣2008

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ሶማያ ክልል ሊገቡ ሲሞክሩ የተገደሉትና በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦብነግ የሽብር ቡዱን አመራሮች ተልእኮውን ከሻዕቢያ መንግስት መቀበላቸውን ተናገሩ ።
በመከላከያ ሰራዊትና በክልሉ ልዩ ሀይል የተገደሉትና የተማረኩት የኦብነግ አባላት በሽቡር ቡድኑ ውስጥ ቁልፍ የአመራርነት ሚና የነበራቸው ናቸው።

ከነዚህ ውስጥም በወቅቱ የተገደለው የሽብር ቡድኑ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ የሎጂስቲክስና የመረጃ ሀለፊዎች ይገኙበታል።

የሽብር ቡድኑ አመራሮቹ በቀደሙት ጊዚያት በክልሉ ህዝብ ላይ በተካሄዱት ዘግናኝ ጭፍጨፋዎች ላይ ትእዛዝ በመስጠት የሚታወቁ ናቸው።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦብነግ የሽብር ቡዱን አመራሮች ለኢቢሲ እንዳሉት ኢትዮጵያ ተዳክማለች በሚል የተሳሳተ መረጃ ምክንያት ኦብነግን ለማጠናከር በማለም ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለመግባት መሞኮራቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ ህዝቦች ሽፍታ በመባል የሚታወቀው የሽብር ቡዱን ባለፈው ጊዚያት በመከላከያ ሰራዊትና በክልሉ ልዩ ሀይል በተወሰደበት ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ ተደምስሷል።

እነዚህ አመራሮች የሽብር ቡድኑ መደምሰስን ተከትሎ ወደ መቃድሾ፣ ኤርትራና ሌሎች ጎረቤት አገራት በመሰደድ ይኖሩ የነበሩ ናቸው።

የአሁኑ የሽብር ተልእካቸውም ከሻዕቢያ ቀጥተኛ ትእዛዝ የተቀበሉበት መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሀመድ ዑመር የኦብነግ አመራሮች መገደልና መማረክ የሽብር ቡድኑ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ሙሉ ለሙሉ ማጣቱን ማሳያ መሆኑን ገልጸው ሁኔታው የኦብነግ፣ የሻዕቢያና የአልሸባብ ግልጽ ግንኙነት የታየበት መሆኑንም ተናግረዋል።
click here to listen the broadcast