Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የአቶ አህመድ ናስር የቀብር ስነ ስርዓት በአሶሳ ተፈፀመ

ahmed nasir
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት የአቶ አህመድ ናስር የቀብር ስነስርአት ዛሬ በአሶሳ ከተማ ተፈፀመ።

በአሶሳ ስታዲየም ለሰዓታት በህዝቡ ስንብት ከተደረገለት በኋላ በከተማዋ በሚገኝ የሙስሊም መካነ መቃብር ቀብራቸው ተፈፅሟል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት፣ የክልል ርእሳነ መስተዳድራን እና የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የአቶ አህመድ አስከሬን ከህንድ ዛሬ ማለዳ ላይ ነበር አዲስ አበባ የገባው።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገዋል።

ለ8 አመታት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት የመሩት አቶ አህመድ ናስር ባጋጠማቸው የኩላሊት ህመም ሳቢያ በህንድ ሃገር በህክምና ሲረዱ ቆይተዋል።

ከትናንት በስቲያ ሌሊትም በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

በርዕሰ መስተዳድርነት ዘመናቸው የክልሉን ሰላም ከማረጋገጥና ልማት ከማምጣት አንጻር ከፍተኛ ስራን ማከናወናቸው ነው የተነገረው።

አቶ አህመድ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባትም ነበሩ።

በርእሰ መስተዳድሩ ሞት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ብሄራዊ ክልሎች ሀዘናቸውን በመግለፅ ለቤተሰብ እና ለክልሉ ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል።benshangul president dies