Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

የኦሮሚያ ክልል 929 የሥራ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

oromo_flag
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 06/2008(ዋኢማ)- የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግሥት በ829 መካከለኛና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ ።

የክልሉ የኮሚንኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለዋልታ እንደገለጹት የክልሉ መንግሥት 121 ከፍተኛ አመራሮች ከደረጃቸው ዝቅ እንዲሉና 708 የሚሆኑት መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል ብለዋል ።

እንደ አቶ ፍቃዱ ገለጻ በመካከለኛና ከፍተኛ አመራሩ ላይ እርምጃ የተወሰደው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ያነሱትን የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎችን መሠረት በማድረግ ነው ተብሏል ።

በአሁኑ ወቅት የመልካም አስተዳደር እጦትን ችግርን መፍታት የሞትና የሽረት ጉዳይ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ፈቃዱ የክልሉ መንግሥት የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰዱን ይቀጥላል አቶ ፍቃዱ አክለው ገልጸዋል ።

የክልሉ ህዝብ በተጨማሪ ከንጹህ ውሃ አቅርቦት ፣ ከመንገድ ልማት ፣ ከጤና አገልገሎት፣ ከቤቶች እንዲሁም ከሥራ አጥነት ጋር በተያያዘ ጥያቄዎችን ማንሳቱን ገልጸው በክልሉ ግንባታቸው ከዓመታት በፊት የተጀመሩ 3ሺ500 የውሃ ፕሮጀክቶች ፣ 52 የመንገድ ፕሮጀክቶችና የ4 ሆስፒታሎች ግንባታ ሥራ መዘግየቱ የክልሉን ህዝብ ውስጥ ቅሬታ መፍጠሩን ተናግረዋል ።

የክልሉ መንግሥት 2ሺ 430 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ፣ 22 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችንና የ4 ሆስፒታሎችን ግንባታ በዘንድሮ የበጀት ዓመት መጨረሻ መወሰኑንና የቀሩትን ፕሮጀክቶችም በሚቀጥለው የበጀት ዓመት ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙን አቶ ፍቃዱ አስረድተዋል ።

ከክልሉ የጤና አገልግሎት ጋር በተያያዘ የክልሉ መንግሥት የተቀናጀ የመድሓኒት ቁጥጥር አሠራርን በመዘርጋት በ20 ሆስፒታሎች ከመዝርጋቱን ባሻገር የጤና ባለሙያዎች ሥልጠና በማመቻቸት የመድሓኒት ብክነትን ችግርን ለማስወገድ ይረዳል ።

በተመሳሳይም የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በተለያዩ ከተማዎች በህገወጥ መልኩ የተያዙ 2ሺ 897 ሄክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ መደረጉንና 1ሺ660 በህገ ወጥ መልኩ የተገነቡ ቤቶች እንዲፈርሱ መደረጉን አቶ ፈቃዱ አያይዘው ገልጸዋል ።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከቀረቡለት ከ45 ሺ በላይ የህዝብ ቅሬታዎች 28ሺ 395 ለሚሆኑት ምላሽ መሥጠቱን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል ።Source :Walta