Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

“የሚዘንብ ዝናብ ላይ ተመርኩዘን መኖር የለብንም” ረዳት ፕሮፌሰር ሳራ ተወልደ ብርሃን

sarah.tewolde-berhan
ዋሽንግተን ዲሲ —
በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ የሚከሰተውን የውሃ እጥረት በተያያዥነትም ረሃብና ድርቅ እንዴት ለመቋቋም እንደሚቻል የተለያዩ የውሃ አጠቃቀም ዘዴዎች ሲተገበሩ ቆይተዋል። የውሃ እጥረት ችግርን በኢትዮጵያ ለመቅረፍ ከዝናብ የምናገኘውን ውሃ በበቂ ሁኔታ እየተንከባከብን የሚዘንበውንም ዝናብ አቁረን በመያዝ ወንዞችና ምንጮች እንዲጎለብቱ በማድረግ ችግሩን ለመቀነስ እንዲሁ ለማስቀረት እንችላለን ስትል በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር፣ እንዲሁም የደንና የምግብ ሳይንስ ባለሙያ ሳራ ተወልደ ብርሃን አስተያየቷን ሰጥታናለች። በአለም አቀፉ የአየርንብረት መዛባትና በኢትዮጵያ እየተከሰት ስላለው የውሃ እጥረት ዙሪያም ችግሩን ለመቅረፍ ምን መደረግ እንዳለበት በአጭሩ አስረድታለች።