Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ኢትዮ ቴሌኮም በቫይበር እና ዋትስ አፕ የተለየ ክፍያ አለመጣሉን ገለጸ

viber and whats upp
መጋቢት 28፣ 2008
በአንደንድ የመገናኛ ብዙሀን ኢትዮ ቴሌኮም በቮይስ ኦቨር አይፒ ማለትም ቫይበር፣ ዋትስ አፕ እና የመሳሰሉት አፕሊኬሽኖች የተለየ ክፍያ ማስከፈል ሊጀምር ነው በሚል የወጡ ዘገባዎች ሀሰት መሆናቸው ኢትዮ ቴሌኮም ገለጸ ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም አድማሴ እንደገለፁት ሰሞኑን መረጃው በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎችና ጋዜጦች በታዘበ መንገድ ቀርቧል፡፡

ህብረተሰቡ እየተጠቀመባቸው ያሉ እንደ ቫይበርና ዋትሣፕ ያሉ የሰልክ ጥሪ አገልግሎቶች ላይ ኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ክፍያ እየጠየቀ አይደለም የማስከፍል እቅድም የለውም ብለዋል፡፡

በሌላ ዜና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ተንቀሣቃሽ ስልኮች በጉምሩክ በኩል እንዲያልፉ የሚደርገው ዘመናዊ የምዝገባ ሥርአት በቅርቡ ይጀመራል ተብሏል፡፡

ይህም ስልክ ቢሠረቅ አልያም ቢጠፋ አገልግሎት እንዳይሠጥ ለማድረግ፤ ጥራት የሌላቸው ስልኮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ለመከላከልና ከውጭ ከሚገቡ ስልኮች ሀገሪቱ ተገቢውን ቀረጥ እንድታገኝ ያስችላል ተብሏል፡፡

አቶ አንዱአለም እንደተናገሩት በቅርቡ የሚጀመረው ዘመናዊ የስልክ ምዝገባ ስርአት ስኬታማ አንዲሆንና ከዚህ በፊት ከውጭ የገቡ ስልኮች ያለምንም ችግር ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ ኢትዮ ቴሌኮም ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ሪፖርተራችን የተመኙሽ አያሌው እንደዘገበችው ጉዳዩን በባለቤትነት ከሚመራው መገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ስለ አሠራሩ በቅርቡ መግለጫ ይሠጣል፡፡