Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል

asmara in voa
VOA Amharic:
በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጠቁመዋል።
eri soldeirs in truck
በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል። በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጠቁመዋል።
በተኩሱና ተያይዘው በደረሱ ጉዳቶች የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ በተለያዩ የተቃዋሚዎች ሚድያ እየተገለጸ ነው። የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ስለሞቱትም ሆነ ስለቆሰሉት ሰዎች በነጻ ምንጭ ማረጋገጥ አልቻለም።

ስለ ጉዳዩ ከኤርትራ ባለስልጣኖች ምላሽም ለማግኘት ሞክረን አልተሳካልንም።Source :VOA