Widgetized Section

Go to Admin » Appearance » Widgets » and move Gabfire Widget: Social into that MastheadOverlay zone

ከደቡብ ሱዳን በመጡ ታጣቂዎች ጉዳት በደርሰባቸው ወገኖች ላይ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው መንግስት ገለፀ

gambela Pm HD
በጋምቤላ እና ደቡብ ሱዳን ድንበር ቀበሌዎች ከደቡብ ሱዳን በመጡ የታጠቁ ሃይሎች በንፁሃን ላይ በደረሰው ጉዳት መንግስት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ ፡፡
ከደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ አባላት የታጠቁ ኃይሎች በአኟና ኑዌር ዞኖች በሚገኙ መኩይ፣ጆር፣ጎግ ጅካዎና ላሬ ወረዳዎች በሚገኙ 13 ቀበሌዎች በፈፀሙት ጥቃት እስካሁን 208 ንፁሃን ሰዎች ለህልፈተ ህይወት ተደርገዋል።

በታጠቁ ኃይሎች ታፍነው የተወሰዱ ህፃናትና እናቶች ቁጥር 108 ሆኗል።

ከደቡብ ሱዳን መጥተው ጥቃቱን የፈፀሙ አካላትን ተከታትሎ ታፍነው የተወስዱ ህፃናትንና እናቶችን ለማስመለስ የኢፌዲሪ መከላከያ ኃይል ጥረትእያድረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልፀዋል። ታጣቂዎችን አድኖ አድኖ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉንም ነው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም የገለፁት።

የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እየወሰዱት ባለው እርምጃ የእስካሁን ጥረትም 60 የሚጠጉ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታውሰዋል።።

የኢትዮጵያ መንግስት ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር በመቀናጀት በአስተዳደራዊና በድፕሎማሲያዊ መንግድ ተመሳሳይ ድርጊቶች እንዳይከሰቱ

እንደሚሰራም ገልፀዋል።

የሱዳን መንግስትም ሆነ የተቃዋሚዎቹ ሀይሎች ከዚህ ጥቃት ጀርባ አለመኖራቸውን መንግስት አረጋግጧል።

መንግስት የጥቃቱ ጉዳት ሰለባ ለሆኑ ዜጎች ድጋፍ እንደሚያደርግም በተለይ ለኢቢሲ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል።

መንግስትም በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘኑን እየገለፀ ለተጎጂ ቤተሰቦች በኢፌዲሪ መንግስት ስም መፅምናናትን ተመኝተዋል።